ትላንት ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ::የካቲት 9 ቀን 2015 ሌሊት 7:51 በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዪ ቦታዉ ቡልቡላ እየባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳ…

ትላንት ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ::

የካቲት 9 ቀን 2015 ሌሊት 7:51 በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዪ ቦታዉ ቡልቡላ እየባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ 10 የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 4 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ አንድ አንቡላንስና 27 የአደጋ መቆጣጠር ሰራተኞቾ የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ተስፋፎቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ዉሏል ተብሏል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ግምትና የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ መሆኑ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መረጃ እንዳመለከተው በአዲስ አበባ የእሳት አደጋዎች እየተደጋገሙና በንብረት ላይም ጉዳት እያደረሱ ይገኛል።

አሁን ያለንበት ወቅት (የአየር ጸባዩ) ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለዉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እሳትና የኤሌክትሪክ ሀይል ምንጮችን በሚጠቀም ጊዜ ከወትሮዉ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁሟል።
በሌላ በኩልም ማናቸዉም አደጋዎች ሲያጋጥሙ አደጋዎች ሳይስፋፉ በ939 የነጻ ስልክ መስመር ፈጥኖ ማሳወቅ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 09 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply