ትላንት ማታ በአቃቂ የገበያ ማዕከል በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 16 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወ…

ትላንት ማታ በአቃቂ የገበያ ማዕከል በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 16 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ ቦቴ ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷአል።

በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ።
አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ
ከተለዩ አንዱ ሲሆን በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።
ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም።
በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply