ትምህርታቸውን በህክምና ዘርፍ የጨረሱ በአማራ ክልል የሚገኙ ሀኪሞች የስራ እድል ይፈጠርልን ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡               ( አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013 ዓ.ም) እንደሚታወ…

ትምህርታቸውን በህክምና ዘርፍ የጨረሱ በአማራ ክልል የሚገኙ ሀኪሞች የስራ እድል ይፈጠርልን ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013 ዓ.ም) እንደሚታወ…

ትምህርታቸውን በህክምና ዘርፍ የጨረሱ በአማራ ክልል የሚገኙ ሀኪሞች የስራ እድል ይፈጠርልን ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013 ዓ.ም) እንደሚታወቀው ሀኪም ለአንድ ሀገር ትልቅ እስተዋጽኦ ማበርክት የሚችልና የዜጎችን ህይወት መታደግ የሚችል አካል ነው፡፡… ስለሆነም የህክምና ትምህርት በሀገራችን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እየተሠጠ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ስዓት ትኩረት እየተሰጠው አለመሆኑን ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ስራ አጥ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ማሳያ በአማራ ክልል የሚገኙ ሀኪሞች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስለሆነም በአማራ ክልል የሚገኙ ትምህርታቸውን በህክምና የጨረሱ ዶክተሮች የስራ እድል ይፈጠርልን ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በባህር ዳር ከተማ የሚኖሩና ከአማራ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰባስበው የስራ እድለ እንዲፈጠርላቸው ያቀረቡት ከዚህ በፊት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ጠይቀው ችግሩን ሊፈታ የሚችል ምንም አይነት ምላሽና ባለማግኘታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው የጠየቁት ሀኪሞች እንደገለጸት በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች ክልሎች የሀኪም ተመራቂ ሆኖ አንድም ስራጥ አለመኖሩን ገልጸው በአማራ ክልል ይህ ሁሉ የህክምና ተመራቂ ስራ አጥ መኖሩ የሚያሳየው የክልሉን ጤና ቢሮ ድክመት ነው ብለዋል፡፡ እኛ የምንፈልገው የኩንትራት ቅጥር ሳይሆን ቋሚ ቅጥር ነው ያሉት ሀኪሞቹ አሁንም የአማራ ክልል መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር መፍትሄ ማስቀመጥ አለበት ሲሉ ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት ለአማራ ክልል ብልጽግና ጽ/ቤትና ለፌደራል የጤና ሚኒስተር መፍትሄ እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት እልባት እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በፊት መንግስት የህክምና ተመራቂ ተማሪዎችን ቶሎ ስራ ይሰጣቸው እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ ግን ይህን ማድረጉን አቋርጦ በየክልሉ ስራ እንድንፈልግና እንድንቀጠር አድርጓል፡፡ ይህ ወደ ሌላ ክልል ሄደን እንዳንሰራ አድርጎናል ለስራ አጥነትም ዳርጎናል ብለዋል ሀኪሞቹ፡፡ አዲስ አባባ ሄደን እንዳንሰራም ተጨማሪ ቋንቋ አለመቻላችን ምክንያት ሆኖብናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል መንግስት ይህንን ከግምት በማስገባት የስራ እድል ይፍጠርልን እኛም ያሳደገን ያስተማረንን ማህበረሰብ በሙያችን እናገልግል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም ስራ አጥ በመሆናቸው ምክንያት ለሞራል ውድቀት እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply