ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ። የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች
ምደባ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ለማየት በድህረገፅ https://result.ethernet.edu.et ፤ በSMS 9444፣ እንዲሁም በቴሌግራም @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ ብሏል።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ሲኖራቸው ደግሞ https://complaint.ethernet.edu.et የሚለውን ድህረገፅ በመጠቀም ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply