You are currently viewing “ትምህርት ሚንስትር በስሜት ሳይሆን        በስሌት ይመራ!”    የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም…

“ትምህርት ሚንስትር በስሜት ሳይሆን በስሌት ይመራ!” የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም…

“ትምህርት ሚንስትር በስሜት ሳይሆን በስሌት ይመራ!” የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም ትምህርት ሚኒሰትር ጥቅምት 2/2015 ከ12 ሽህ በላይ የአማራ ተማሪዎች ፈተናውን አቋርጠው ወጥተዋል በሚል በተማሪዎች ላይ የሰጠውን የፈጠነ ውሳኔን በማውገዝ ተቋሙ ከስሜት ይልቅ በስሌት እንዲመራ ጠይቋል። ትምህርት የድህነትን ተራራ የምንንድበት ከድህነት ቀንበር የምንላቀቅበት የህልማችን ጨለማ ግርዶሽ ወደ ብርሀን የሚቀየርበት ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡ ትምህርት ነገን ዛሬ የምንሰራበት የህይወታችን መወሰኛ ነው፡፡ በተለይም 12 ዓመታትን በትምህርት ዓለም ያሳለፈ ሰው የ12ኛ ክፍልን ፈተና ተፈትኖ አዲሱን የዩንቨርስቲ ዓለም ለመቀላቀል በጉጉት የሚናፍቅበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ መሰረትም የኢፌዲሪ ትምህርት ሚንስትር አዲስ በዘረጋው የፈተና አሰጣጥ መርሀ ግብር በመላው ሀገራችን የተውጣጡ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለምዘና በተቀመጡበት ፈተና፣ ከአራት የፈተና ማዕከላት ወደ 13 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን አንወስድም በማለት ሳይፈተኑ መቅረታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በባሕር ዳር እና በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች መፈተን ከነበረባቸው ተማሪዎች መካከል 12 ሺህ 787 ተማሪዎች የተወሰኑትን ፈተና ወስደው ወይም ሙሉ ለሙሉ ከፈተናው እራሳቸውን አግልለዋል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ክስተት “ከትምህርት ሥርዓቱ ያፈነገጠ ነው” ያለ ሲሆን፣ አንፈተንም በማለት ከፈተና ማዕከላቱ ለቀው የወጡ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ያደረጉት በመሆኑ ሌላ የፈተና ዕድል እንደማይኖራቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም በተለይ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኃይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ፈተናውን ለማስተጓጎል በፈጠሩት ግርግር የአንድ ተማሪ ሕይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። በመጀመሪያው ዙር የ2014 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 595 ሺህ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ 586,541 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረትም የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል፤- 1. ትምህርት ሚንስትር የዘረጋው አዲስ የፈተና አሰጣጥ ስርዓት የሚደነቅ ቢሆንም በቅድመ ዝግጅት፤በትግበራና፤በማጠቃለያ ምዕራፍ ከፍተኛ የዝግጅት፤የአሰራር፤ የመናበበብ ችግር የነበረበት ምቹ የፈተና አሰጣጥ ስርዓት በተለይም በስም በተጠቀሱ ዩንቨርስቲዎች በጉልህ የተስተዋለ መሆኑን መረጃ የደረሰን በመሆኑ ችግሮችን ሁሉ ለተማሪ መስጠት ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ትምህርት ሚንስትር አሰራሩን እንዲፈትሽ እንጠይቃለን፤ 2. በአማራ ክልል ብቻ የተፈጠረውን ችግር በጥቅል ስረ ነገሩ ወይም ምክንያቱ በዝርዝር ሳይጣራ ከትምህርት ስርአት አፈነገጠ በማለት በተለይም አንድን ትውልድ መፈረጅ በራሱ ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥተን የምንከታተለው ሁኖ 13 ሽህ ተማሪን በስሜት አልፈትንም ብሎ ወጥቶል ብሎ መግለጫ መስጠት ያልተጠና፤ያልተገመገመ፤ ግለሰባዊ ውሳኔ በመሆኑ በአስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን፤ 3. በአዲስ ነባራዊ ሁኔታ እና አካባቢያው ሁኔታ ከቤተሰቦቻቸው ጉያ ሳይወጡ ላደጉ ተማሪዎች አዲሱ የፈተና አሰጣጥ ሁኔታ ጭንቀት፤ መደናገጥን እንዲሚፈጥር ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በመጀመሪያው ዙሩ የተከሰቱ ችግሮችን ላለመድገም ትምህርት ሚንስተር እኔ ብቻ አውቃለሁ ከሚል ግትር ስሜት ወጥቶ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ እንዲሰራ ምክረ ሀሳብ እንሰጣለን፤ 4. ትምህርት ሚንስትር ለተፈጠረው ችግር ከስሜታዊነት በጸዳ መንገድ በብስለት ውሳኔውን እንደሚስተካክል እየተማመን ይህ ግትር አቋም ከጸና ግን በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው ሁለተናው ጥቃት በትምህርት ዘርፉ ከጥላቻ ጋር ተዋህዶ የፖለቲካ ደባና ተንኮል ያለበት መሆኑን በማመን ሁለተናዊ ትግል የምናደርግ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ 5. በመጨረሻም በተከሰተው ችግር ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑር እያልን ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እየተመኘን ትምህርት ሚንስትር የሀዘን መግለጫ ባለመስጠቱ እናፍራለን፡፡ በስሜት ሳይሆን በስሌት መስራት ይበጃል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply