ትሪ ቢየን “ህጋዊ ሆኜ በሀገሪቱ ሁለት ብቻ የፀጉር ንቅለ ትከላ የሚሰጡ ክሊኒኮች አሉ መባሉ ” ችግር ፈጥሮብኛል አለ

ትሪ ቢየን  “ህጋዊ ሆኜ  በሀገሪቱ  ሁለት ብቻ   የፀጉር ንቅለ ትከላ የሚሰጡ  ክሊኒኮች  አሉ መባሉ  ”  በደንበኞቼና በገበያዬ ላይ ችግር ፈጥሮብኛል አለ

ቦሌ መዳያአለም ሸገር ህንፃ ላይ የሚገኘው  ትሪ ቢየን ልዩ የቆዳ ክሊኒክ የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን  ለፀጉር ንቅለ ተከላ  ህጋዊ ፍቃድ ሰጥቶን   በአግባቡ እየሰራን  ሳለ  በባለስልጣን መ/ ቤቱ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ   ”   በከተማዋ ህጋዊ የሆኑ ሁለት የፀጉር ንቅለ ትከላ  ክሊኒኮች  ያሉት ” ማለቱ    እጅግ አሳፋሪ ነው ሲሉ  የክሊኒኩ ስራ አስኪያጅ  ዶ/ ር ቅድስት የኔነህ  ዛሬ በሰጡት መግለጫ  አሳውቀዋል።

”  ከመንግስት ፍቃድ አግኝተን ከቱርክ ባስመጣነው ዶክተር የፀጉር ንቅለ ተከላ   እያካሄደን  ነበር። መንግስት ግን እኛ ፍቃድ ያልሰጠን ይመስል ሌሎች ሁለት ክሊኒኮች ብቻ ናቸው  ፍቃድ  ያላቸው ማለቱ   ደንበኞቻችን ላይ ጥርጣሬ ከመፍጠሩም ባሻገር  ገበያችን ላይ ችግር ፈጥሯል ” ብለዋል።

ዶ/ ር ቅድስት አክለውም ”  ባለስልጣን  መ/ ቤቱ  ይቅርታ ጠይቆ ተገቢውን ማስተካከያ  ” ያድርግም ሲሉ ጠይቀዋል።

The post ትሪ ቢየን “ህጋዊ ሆኜ በሀገሪቱ ሁለት ብቻ የፀጉር ንቅለ ትከላ የሚሰጡ ክሊኒኮች አሉ መባሉ ” ችግር ፈጥሮብኛል አለ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply