ትራምፕ ከቻይና የወታደራዊ መስራያ ቤት ጋር ግንኙነት ባላቸው ድርጅቶች ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ኢንቨስት እንዳያደርጉ አገዱ

ትራምፕ ከቻይና የወታደራዊ መስራያ ቤት ጋር ግንኙነት ባላቸው ድርጅቶች ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ኢንቨስት እንዳያደርጉ አገዱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና የወታደራዊ መስራያ ቤት ጋር ግንኙነት አላቸው ባሏቸው ድርጅቶች ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ኢንቨስት እንዳያደርጉ አገዱ፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ያገዳቸው ድርጅቶች 31 ናቸውም ተብሏል፡፡

ከነዚህ መካከል ግዙፉ የስማርት ስልኮች አምራቹ ህዋዌ ኩባንያ እንደሚገኝበት ተገልጻል፡፡

እገዳው ከኩባያዎቹ ጋር ከመገበያየት በተጨማሪ በባለቤትነት መያዝንም ይከለክላል ነው የተባለው፡፡

የቻይና ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ድርጊቱን የኮነነው ሲሆን ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ የቻይና ኩባንያዎችን ለመጉዳት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

እገዳው የተላለፈባቸው አንዳንዶቹ ኩባንያዎች ወቀሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከቻይና ወታደራዊ ተቋም ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ጠቅሰዋል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር የወሰነው ውሳኔ ከታህሳስ መጀመሪያ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተሰምቷል፡፡

 

 

ምንጭ፡-ሲኤንኤን

 

The post ትራምፕ ከቻይና የወታደራዊ መስራያ ቤት ጋር ግንኙነት ባላቸው ድርጅቶች ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ኢንቨስት እንዳያደርጉ አገዱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply