ትራምፕ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶማሊያ እንዲወጡ አዘዙ – BBC News አማርኛ

ትራምፕ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶማሊያ እንዲወጡ አዘዙ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/43D0/production/_115806371__115805358_gettyimages-51350988.jpg

ለሦስት አስርታት ያህል በእርስ በርስ ጦርነትና ባለመረጋጋት ውስጥ በቆየችው ሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዘዋል። የደኅንነት አማካሪዎች ግን በአካባቢው ያሉ ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድኖችን የሚያበረታታ ነው በሚል ውሳኔውን ተቃውመውታል። ትራምፕ ከሶማሊያ በተጨማሪ በኢራቅና በአፍጋኒስታን የሚገኘው የአሜሪካ ሠራዊት ቁጥር እንዲቀንስ አዘዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply