ትናንት ሌሊት በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከ14 በላይ አማራዎችን በግፍ የገደሉት አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ    የሟቾችን ስርዓተ ቀብር ለማደናቀፍ ጥረት አድርገው እንደነበር ተገለፀ።…

ትናንት ሌሊት በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከ14 በላይ አማራዎችን በግፍ የገደሉት አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የሟቾችን ስርዓተ ቀብር ለማደናቀፍ ጥረት አድርገው እንደነበር ተገለፀ።…

ትናንት ሌሊት በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከ14 በላይ አማራዎችን በግፍ የገደሉት አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የሟቾችን ስርዓተ ቀብር ለማደናቀፍ ጥረት አድርገው እንደነበር ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ… ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሚመሩት ኦሮሚያ ክልል በተለይም በወለጋ እና በሆሮ ጉድሮ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በአማራ ላይ የሚፈፀመው የለየለት ማንነት ተኮር ግፍ እና በደል ዛሬም መቋጫ አላገኘም። እንደአብነትም ትናንት ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 1 እስከ 6 ሰዓት ድረስ በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ በተባለ ቀበሌ የጦር መሳሪያ እና ገጀራ የተሸከሙ ከፍቅርና አብሮነት ይልቅ በሕወሓትና በኦነግ ጥላቻና የሀሰት ትርክት ተኮትኩተው ያደጉ ፅንፈኞች አማራ በመሆናቸው ብቻ እመጫት፣ህጻናትና አዛውንቶችን ጨምሮ በ14 አማራዎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ከጭፍጨፋው ያመለጡ ነዋሪዎች እንደገለፁትም ታጣቂዎቹ ለተከታታይ 3 ቀናት በአካባቢው ሲሰበሰቡ ተመልከተው ስጋት ስለገባቸው መንግስት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቢይጠይቁም ውሸት ነው በማለት በወረዳው እና በልዩ ሀይሉ ሰሚ በማጣቸው ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። በግፍ ከተገደሉት መካከልም ካሴ ባየ፣ ሙሳ ደርሶ፣ ይብሬ አድማሱ፣ ደመቀ ጎባው፣ ፋጢማ ይብሬ፣ አሚድ ይብሬ፣ ማሪፋ ይብሬ፣ ሀሰን ይብሬና አደም አበባው ይገኙበታል። በፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ አቋማቸው ከጣሊያን ጋር የሚመሳሰሉት ፅንፈኞቹ በገደሏቸው ንፁሃን አማራዎች ስርዓተ ቀብር ላይ በመገኘት ቦንብ ለመጣል ያደረጉት እንቅስቃሴ በሚሊሻዎች ተሳትፎ መክሸፉ ተጠቅሷል። አሁንም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግድያ፣ እስርና ማፈናቀል እንዲቆም የጠየቁት ነዋሪዎቹ የክልሉ መንግስት ውስጡን እንዲፈትሽና እንዲያስተካክል ጠይቀዋል። የክልሉ መንግስትም ሆነ ልዩ ሀይል እውነተኛ ለውጥ የሚፈልግ ከሆነ ለነፍሰ ገዳዮች ከመወገን ይልቅ በክልሉ ያሉ አማራዎችን እንደ ዜጋ ቆጥሮ እንዲታደጋቸው ጥሪ ቀርቧል። የፌደራል መንግስት በአካባቢው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር እና በአሸባሪዎች ላይ እርምጃ የሚወስድ የመከላከያ ሰራዊትን እንዲያሰማራ፤ የአማራ ክልል መንግስትም በማንነታቸው እየተጠቁ ያሉ ወገኖችን በተቆርቋሪነት ስሜት እንዲታደጋቸው፣ተባብረው የተፈናቀሉትን ወገኖች መልሰው እንዲያቋቁማቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply