ትናንት ማታ በባህርዳርና በጎንደር አዘዞ የተሰማው ፍንዳታ የህወሃት ሮኬት መሆኑ ተገለጸ፡፡            አሻራ ሚዲያ       ህዳር 05 /2013 ዓም ባህር ዳር  ትላንት 5:00 ሰዓት…

ትናንት ማታ በባህርዳርና በጎንደር አዘዞ የተሰማው ፍንዳታ የህወሃት ሮኬት መሆኑ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር 05 /2013 ዓም ባህር ዳር ትላንት 5:00 ሰዓት…

ትናንት ማታ በባህርዳርና በጎንደር አዘዞ የተሰማው ፍንዳታ የህወሃት ሮኬት መሆኑ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር 05 /2013 ዓም ባህር ዳር ትላንት 5:00 ሰዓት ገደማ በባህር ዳር መኮድ እና በጎንደር አዘዞ አካባቢ በተቀራራቢ ሰአት መለስተኛ ፍንዳታ እንደተፈፀመ የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡ “የተከበራችሁ የክልላችን ህዝቦች አሁን ምሽት ላይ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ የተፈጠረ ፍንዳታ የነበረ ቢሆንም ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነውም ተብሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በከተማችን የተለየ የመብራተ መቆራረጥ አልተፈጠረም፡፡ ከተማችን በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ፍንዳታው ከጁንታው ቡድን የአጥፍቶ ጠፊነት የሽብር ተግባር ጋር ስለመገናኘት አለመገናኘቱ መረጃዎቹ በሚመለከተው አካል በመጣራት ላይነው። የጠላት ኃይል ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሽብር ስራ እየሰራ ስለሆነ ጦርነት ውስጥ ያለን መሆኑ ታውቆ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እራሱንና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የክልሉ መንግስት አሳስቧል፡፡ በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊቶች ሊፈፀሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠበቅ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ትናንት ምሽት ወደ ባህርዳርና ጎንደር ከተሞች ሮኬት ተተኩሶ እንደነበር ተነገረ። በዚህም የአየር ማረፊያ አካባቢዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ለዚህም “የህወሓት ጁንታ” ያለውን የመጨረሻ መሳሪያዎች እየተጠቀመ ይገኛል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ክፍል አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply