ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የተሰበሰበው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አ…

ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የተሰበሰበው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በህወሀት ላይ እየተወሰደ ስላለው በጦርነት የታገዘውን ህግ የማስከበር እርምጃን በተመለከተ ትናንት ሌሊት በመንግስታቱ ድርጅት ዋና መቀመጫ ኒዮርክ ተሰብስቦ እንደነበር ተገልጧል። ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ቀደም ሲል ይዞት ለነበረዉ ቀጠሮ የአፍሪቃ ሐገራት ድጋፍ ባለመስጠታቸው ምክንያት ሰርዞት ነበር ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ይሁንና በምክር ቤቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉ ፈረንሳይና ብሪታንያን፣ ጨምሮ የአዉሮጳ ሐገራት ዉይይቱ እንዲደረግ ግፊት በማድረጋቸዉ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዙሪያ መሰብሰባቸው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ብሏል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘዉ ጦርነት በርዕስነት እንዲቀርብ ከፈረንሳይና ከብሪታንያ በተጨማሪ ግፊት ያደረጉት ቤልጂየም፣ ጀርመንና የወቅቱ የጸጥታው ምክርቤት ተለዋጭ አባል የሆነችው ኢስቶኒያ ናቸዉ። አፍሪካን ወክለው የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የሆኑት ደቡብ አፍሪካ፣ኒጀር እና ቱኒዝያ የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች ሥለገጠሙት ጦርነት መረጃ የሚያሰባስብ የመልዕክተኞች ጓድ ወደ ኢትዮጵያ መሔድ አለበት በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለዉይይት መቅረቡን ተቃውመዋል። ይሁንና በመጨረሻም ስብሰባው ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው የትኛውም አገር በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply