
ትናንትና በጎንደር ከተማ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ግጭት ተቀስቅሶ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተገለጸ። የክልሉ መንግሥት ትላንት ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ. ም. አመሻሹን ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ሳቢያ ሰዎች እንደሞቱ፣ የአካል ጉዳት እንደደረ እና ንብረትም እንደወደመ ገልጿል። ነገር ግን ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ እና ምን ያህል ንብረት እንደወደመ በዝርዝር አልተገለጸም።
Source: Link to the Post