#ትኩረትበሃኪም ማዘዣ የሚሰጡ መድሃኒቶችን በሰዓቱ አለመውሰድ እና ጀምሮ ማቋረጥ የሚያስከትሉት ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፡-የጤና እክል ሲያጋጥም ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ ከተደረገ በኋ…

#ትኩረት

በሃኪም ማዘዣ የሚሰጡ መድሃኒቶችን በሰዓቱ አለመውሰድ እና ጀምሮ ማቋረጥ የሚያስከትሉት ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፡-

የጤና እክል ሲያጋጥም ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ለህመሙ ፈዋሽ የሆነ መድሀኒት በሃኪም ይታዘዛል፡፡
የታዘዘውን መድሀኒት ለመግዛት ወደ መድሃኒት መሸጫ መደብሮች በማምራት በመግዛት ከህመሙ ለመዳን ጥረት ይደረጋል፡፡

ታዲያ ፋርማሲስቶች የሚሰጡትን መመርያዎች በመገንዘብ መድሃኒቶችን በአግባቡ የሚወስዱ ቢኖሩም ፤ አንዳንዶች ግን ይህን ተግባራዊ እንደማያደርጉት ይነገራል፡፡ በአንጻሩ መድሀኒት ለመግዛት አቅም አንሷቸው ከህመማቸው ለመዳን የሚቸገሩ፤ ህይወታቸው እንዳያልፍ የወዳጅን ዘመድ እጅ የሚመለከቱ መኖራቸው ሲነገር ይደመጣል፡፡

በከፍተኛ ዋጋ በውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድሃኒቶችን በመግዛት ጀምረው የሚያቋርጡ መኖራቸውም ይገለጻል፡፡

ወ/ሮ አስቴር ከተማ ፋርማሲስት ናቸው፡፡ በመንግስት ሆስፒታል፣ በከነማ እና በተለያዩ የግል መድሃኒት መደብሮች በፋርማሲስት ሞያ ከ40 አመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፤ አሁን በብሩክ መድሃኒት መደብር በሀላፊነት እየሰሩ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው፡፡

“የፋርማሲ ሞያ ትልቅ ሃላፊነትን የሚጠይቅ ነው፡፡ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት አደራ አለብን”የሚሉት ወ/ሮ አስቴር ሰዎች መድሃኒት ሲገዙን አመኔታቸውን እኛ ላይ በመተው ነው ሲልም ተናግረዋል፡፡

መድሃኒቶችን ለመግዛት የመድሃኒት ማዘዣ ይዘው አልያም ያለ መድሃኒት ማዘዣ ወደ መደብራቸው ታማሚዎች እንደሚሄዱ የነገሩን ሲሆን፤ የመድሃኒት ማዘዣ ይዘው ሲመጡት ግን መቋረጥ የሌለባቸውን መድሃኒቶች እንዳያቋርጡ እና ከተቋረጠ የሚያስከትሏቸው ተጓዳኝ ችግሮችን አጥብቀን እንናገራለን ነው ያሉት፡፡

#በሃኪም ማዘዣ የሚሰጡ መድሃኒቶችን በሰዓቱ አለመውሰድ እና ጀምሮ ማቋረት የሚያስከትለው ችግር

 በሽታውን ያመጡጥ ባክቴሪዎች እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች በሽታውን እንዲላመዱ ያደርጋል
 የመዳን አቅምን የማዳከም ሁኔት እንደሚኖር ተመላክቷል፡፡

#በሃኪም ማዘዣ የሚወሰዱ መድሃኒቶችን ጀምሮ ለማቋረጥ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው፤

-የሚስተዋሉ የህመሙ ምልክቶች የመሻሻል ለውጥ ሲመለከቱ
-በሃኪም የሚታዘዘውን የመድሃኒት መጠን አለመግዛት
-የመድሃኒት መዋጫ ሰዓት መዘንጋት
-በዋነኝነት ግን የሰዎች ግዴለሽነት መሆኑም ነው ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ወ/ሮ አስቴር በሃኪም የሚታዘዙ መድሃቶችን ጀምሮ በማቋረጥ ምክንያት ህመማቸው ይበልጥ ጠንክሮ እና ተባብሶባቸው ሲመጡም እናስተውላለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

መድሃኒቶችን በሰዓት እና መጠን ያለማቋረጥ ሊወሰዱ ይገባል፤ ይህም መድሃኒቱ በደማችን ውስጥ በመቆየት የህመሙን መነሻ ምክንያቶች ለማከም እና ከህመሙ ለመዳን ይረዳል ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች ሲወስዱ ከመዘናጋት ይልቅ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፤የፋርማሲ ባለሞያዎችም በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ልናስረዳ ይገባል ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply