ትኩረት ለሸዋ ቀጠና አምስተርዳም :- ሐምሌ 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአማራ ህዝብ እጅግ አስከፊው የአገዛዝ ዘመን ውስጥ መሆኑን መናገር ለቀባሪ…

ትኩረት ለሸዋ ቀጠና አምስተርዳም :- ሐምሌ 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአማራ ህዝብ እጅግ አስከፊው የአገዛዝ ዘመን ውስጥ መሆኑን መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው። ሰሞናዊ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት መንግስታዊ እና መዋቅራዊ ጥቃቱ ከወለጋ እና አካባቢው አልፈው አማራ ክልል ውስጥ ሆኗል። የብልፅግና መንግስት የአማራን ህዝብ በታሪክ ህልውናው ስጋት ውስጥ ከቶታል። በዚህም ለተከታታይ 4 ዓመታት መንግስታዊ ጥቃት ፈፅመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወድህ በሸዋ ህዝብ ላይ የሚደረጉ መንግስታዊ ሺብሮች መነሻቸውም መድረሻቸውም መንግስታዊ ጥቃት ነው። የአማራን ህዝብ ዕረፍት መንሳት እንደ ግብ የቆጠረው የብልፅግና መዋቅር አሁንም ተጨማሪ ስጋት በሰ/ሸዋ አካባቢዎች ምልክት እየታየ ነው። ሸኔ በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛውን የዘርጭፍጨፋ ያደረገው የኦሮሞ ብልፅግና መዋቅርን እየተጠቀመ መሆኑን ከራሳቸው ከብልፅግና የህዝብ ኢንደራሲዎች ተሰምቷል። ስለሆነም ሰሞኑን በአጣየ የተደረገው የሺብር ድርጊት የሸዋን ህዝብ ማጥቃት ነው። ከመንግስት መዋቅሩ ጋር በመሆን ዋጋ የከፈለውን ልዩ ሃይል ህጋዊ እርምጃ አለመውሰድ በተጨባጭም የህልውና ስጋታችን ዕረፍት እንደሌለው የሚያሳይ ነው። ስለሆነም የኦሮሙማው ፕሮጀክት ማስተር ማይንዶች በሸዋ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ውንጀላዎችንና ጦርነቶች ለማድረግ በትጋት እየሰሩ ስለመሆኑ በግልፅ እየታየ ነው። ከአዋሺ መልካሳ የተነሳው የአሸባሪው ሸኔ ክንፍ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ያንጋሃም አካባቢ ከሰለጠኑ በሗላ በአፋር አድርጎ ወደፊት ሸዋሮቢት የገባው ይሄው ሃይል የፌደራል እና የመከላከያ አልባሳትን እየተጠቀመ ተደጋጋሚ ጥቃትን እየፈፀሙ ናቸው። ስለሆነም ተቋማዊ የፀጥታ መዋቅር አልባሳትን በመልበስ ለሺብር እንድሰራ እያደረገው ያለው መንግስታዊ መዋቅሩ መሆኑን በእርግጠኝነት እንድናምን ሆነናል። ስለሆነም በታሪክ የወሰን ተጋሪው የሆነው የሸዋ ህዝብ ፀጥታው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል። በቡድን መጓተት እና በጥሬ ስልጣን ምክንያት የሸዋ ከተሞች መውደም የለበትም። ህዝብን ለፍትህ ፍጆታ እየዋሉ በስልጣን መቀጠል አይቻልም!! አሁንም ትኩረት ለሸዋ አካባቢ ቀጠናዎች እንድሆንና ማህበረሰቡን ከአላስፈላጊ መዘናጋት እንድወጣ ይደረግ!! በተለይ ምንጃር፣ሸዋሮቢት፣አጣየ እና ቡልጋ ከተማ አስተዳደር የዘወትር ጥንቃቄ እና ወትሮ ዝግጁ መሆንን የሚጠይቁ ናቸው። ምንጊዜም መንቃት!! ©አሸናፊ ገናን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply