
“ትክክለኛ ጉልበት ከባለ ታንኩ ከባለ መትረጌዬሱ እጅ አይደለም፤ ትክክለኛው ጉልበት ያለው ህዝብ እጅ ላይ ነው።” (አርበኛ ዘመነ ካሴ) “ፍርሃት እንደ ጅብራ ከፊትህ ተገትሮ ካየህው ተጋፈጠው፤ ደፍጥጠው። ገፍተህ ጣለው። ምክንያቱም ፍርሃት በበዛበት አካባቢ ነጻነት ተደብቃለች ማለት ነውና! ከፍርሃት ግድግዳ ግልባጭ ነጻነት ቆማለች። የፍርሃት ግድግዳን በወኔ እና በልበ ሙሉነት መዶሻ አፍርስ፤ ያኔ ነጻ ትወጣለህ። ትክክለኛ ጉልበት ከባለ ታንኩ ከባለ መትረጌዬሱ እጅ አይደለም፤ ትክክለኛው ጉልበት ያለው ህዝብ እጅ ላይ ነው። አሳዛኙ ነገር ህዝብ ያለውን እምቅ አቅም በቅጡ አይረዳም። ህዝብ ባለበት ቆሞ ፊቱን በማዞር ብቻ ወይንም የዐይኑን እንቅስቃሴን በመቀዬር ብቻ መንግስት የሚባለውን ቡድን ማፍረስ ይችላል። ይህ ተፈጥሮአዊ ሀቅ ነው። ይህን ለህዝብ ደጋግሞ መንገር ያስፈልጋል። የህዝብ ድምጽ የአምላክ ድምጽ ነው። ህዝብ ፊቱን ሲያዞርብህ አምላክ ነው ፊቱን የሚያዞርብህ። ህዝብ ጠላህ አምላክ ጠላህ። አንድነት፣ አንድነት፣ አንድነት!” ለወንድሜ ዓባይ ዘውዱ (አማራ ሚዲያ ማዕከል) ዘመነ ካሴ ከባህር ዳር ወህኒ ቤት! መልካም ልደት ለአርበኛ ዘመነ ካሴ! ፍትህ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ፣ ደብረ ብርሃንን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ እስር ላይ ለሚገኙ ፋኖዎች፣ ለጸጥታ አካላት፣ ለጋዜጠኛ እና ታሪክ ጸሀፊው ለታዲዎስ ታንቱ እንዲሁም ፍትህ ለሁሉም ይሁን!
Source: Link to the Post