ትውልደ ላቲን አሜሪካ ወጣቶች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲከተቡ ለማበረታታት የሚደረግ ጥረት

https://gdb.voanews.com/10070000-0aff-0242-fdde-08da5f8b989f_tv_w800_h450.jpg

በዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ክፍል ግዛት ጸረ ኮቪድ 19 ክትባት የሚከተቡ የላቲን አሜሪካ ዝርያ ወጣቶች ቁጥር ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ያንሳል። በዚህም ምክንያት ወጣቶቹ ክትባቱን እንዲወስዱ ለማበረታታት ዘመቻ እየተካሄደ ነው። 

የኮሎራዶ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እንዲከተቡ ለማበረታታት በሚደረጉት የዘመቻ እንቅስቃሲዎች ከተሳተፉት መካከል አንዷ ሞንሲራት ሜንዶዛ የምትባል የአስራ ስድስት ዓመት ወጣት ሰዐሊ ስትሆን የሞንሲራት ስዕሎች በዴንቨር ከተማ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች እና የአውቶቡስ ፌርማታዎች ላይ  በብዛት ይታያሉ።

ሞንሲራት ስዕሎቿን በስፓኝ ቋንቋ “አ ቪቪር ኮን ላ ቫኩና” ሲተረጎም “ይከተቡ እና ረጅም ዕድሜ ያግኙ” ብላ የሰየመቻቸው ሲሆን በስዕሎቿ አማካይነት የምታስተላለፈው መልዕክት ማኅበረሰቧን ያበረታታል ብላ ተስፋ ታደርጋለች።

ከዴንቨር ከተማ ስቪትላና ፕሪስቲኒስካ ያጠናቀረችው ዘገባ ነው። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply