You are currently viewing ትውልድ የማይረሳው ለአማራ የተከፈለ የነሃሴ 5ቱ ታላቅ የክብር መስዋዕትነት!_ጀግኖቹ ፋኖ ቻላቸው እንዬው፣ ፋኖ ፍቅሬ ተመልካችና ሌሎች የትግል ጓዶች ደብረ ዘቢጥ ላይ የተሰውበት ቀን! አማራ…

ትውልድ የማይረሳው ለአማራ የተከፈለ የነሃሴ 5ቱ ታላቅ የክብር መስዋዕትነት!_ጀግኖቹ ፋኖ ቻላቸው እንዬው፣ ፋኖ ፍቅሬ ተመልካችና ሌሎች የትግል ጓዶች ደብረ ዘቢጥ ላይ የተሰውበት ቀን! አማራ…

ትውልድ የማይረሳው ለአማራ የተከፈለ የነሃሴ 5ቱ ታላቅ የክብር መስዋዕትነት!_ጀግኖቹ ፋኖ ቻላቸው እንዬው፣ ፋኖ ፍቅሬ ተመልካችና ሌሎች የትግል ጓዶች ደብረ ዘቢጥ ላይ የተሰውበት ቀን! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ነዋሪነቱ በጎንደር ቀበሌ 18 የነበረው ጀግናው እና ደፋሩ ፋኖ ቻላቸው እንዬው የአማራው እምብርት ወሎ በአሸባሪው እና ወራሪው ትሕነግ ተደፈረ፣ ጠላት ወደ ሰሜንና ደቡብ ጎንደርም እየገሰገሰ መሆኑን የተገነዘቡት ጀግኖቹ እነ ፋኖ ቻላቸው እንዬውና ጓዶቹ ከጎንደር ተነስተው ጠላት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ቀጠና አምርተው ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በወቅቱ ያሰባሰበው መረጃ እንዳመለከተው ደብረ ዘቢጥ በተባለ ግንባር ከተሰለፉት መካከል ፋኖ ቻላቸው እንዬው እና ፋኖ ፍቅሬ ተመልካች ነሃሴ 5 ቀን 2013 አማራን ለመውረር የመጣ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለሚወዱት እና ለሚታገሉለት ለአማራ ህዝብ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት በክብር መስዋዕት የሆኑበት ጥቁር ቀን ነበር። በእርግጥ ታጋይ ይሞታል፤ ትግል ግን መቀጠሉ የነበረ፣ ያለ እና የሚቀጥል እውነታ በመሆኑ በዚያ የሃምሌ እና የነሃሴ 2013 ሰሞን ጠላትን ያንበረከኩ በርካታ እንቁ የአማራ ልጆችን ያጣንበት ሰሞን ነበር። በዛን ወቅት ወታደራዊ ግዳቸውን በጀግንነት የፈጸሙ እና መጨረሻም ራሳቸውን፣ ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው እስከመስጠት ከወደዱን የአማራ ፋኖ አባላት በጎንደር እንደማሳያ የሚከተሉት ይገኙበታል። በሁለተኛው ዙር መከላከያ መቀሌን ለቆ ከወጣ ከሰኔ 23/2013 በኋላ በተፈጸመው ወረራ ወቅት በተደረገ ተጋድሎ ከተሰው ጀግኖች መካከል:_ 1) ቻላቸው እንዬው፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 18 ሲሆን የተሰዋው_ነሃሴ 5 ቀን 2013 ደብረ ዘቢጥ ላይ ነው። 2) ፍቅሬ ተመልካች፣ ነዋሪነቱ_ ጎንደር ቀበሌ 18 የተሰዋው_ ነሀሴ 5 ቀን 2013 ደብረ ዘቢጥ ላይ ነው። 350 ሽህ ብር ስናይፐር በግል ገንዘቡ ገዝቶ የዘመተ የጀግናው፣ ወያኔ ያስገደለው የአቶ ዳኛቸው ተመልካች ወንድም ነው። 3) ደሞዝ ማንነገረው፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 18 የተሰዋው_ነሃሴ 3 ቀን 2013 ደብረ ዘቢጥ ላይ ነው። 4) አሸናፊ ሙሃባው፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 18 የተሰዋው_ ደብረ ዘቢጥ ላይ ነው። 5) ህርያቆስ አበበ፣ ነዋሪነቱ _ጎንደር ቀበሌ 3 የተሰዋው_ ነሀሴ 4 ቆስሎ በአዲስ አበባ የህክምና ክትትል ሲደረግለት ቆይቶ ነሃሴ 18/2013 ያረፈ ጀግና ነው። የተመታው ደብረ ዘቢጥ ላይ ነው። በአሸባሪው ትሕነግ በግፍ በእስር ቤቱ ከተሰቃዩት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል አንዱ ነበር። 6) አዳነ ጎሸ፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ አካባቢ፣ የተሰዋው_ሀምሌ 16 ቀን 2013 አዳርቃይ ማይልሃም 7) ሐፍቴ ኪዴ፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ የተሰዋው_ሀምሌ 16 ቀን 2013 አዳርቃይ ማይልሃም ነው። 😎 ምስጋናው፣ ነዋሪነቱ _ጎንደር አዘዞ መገንጠያ የተሰዋው_ሀምሌ 16 ቀን 2013 አዳርቃይ ማይልሃም ነው። 9) መኳንንት እርታቸው፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 16 የተሰዋው_ነሃሴ 26 ቀን 2013 ደባርቅ ዳባት_ወቅን አካባቢ ነው የተሰዋው። 10) እንዳለው ፍቃዴ (ያየሽ)፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር የፋኖ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረ። የተሰዋው_ነሃሴ 13 ቀን 2013 ደባርቅ ዳባት መስመር ቦዛ ላይ የተሰዋ። 11) ፋሲል ፈንቴ፣ ነዋሪነቱ_ጎንደር ቀበሌ 18 የተሰዋው_ነሃሴ 27 ቀን 2013 ከቀኑ 11 ሰዓት የቆሰለ፣ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 በጎንደር ሆስፒታል ያረፈ። የተመታውም ጭና ተክለ ሀይማኖት አካባቢ ነበር። 12) አምላኩ መስታይት፣ ነዋሪነቱ_ ከወረታ ካምፕ እየተመላለሰ ከእናቱ ጋር ጎንደር ብልኮ ይኖር የነበረ። በወያኔ እስር ቤት ለ4 ዓመታት የተሰቃዬ፣ ኤርትራ በርሃ ድረስ የዘመተና የታገለ፣ ከእስር እንደተፈታ ለሁለተኛ ዙር ኤርትራ በርሃ የሄደ ጀግና ነበር። የተሰዋው_ሀምሌ 15 ቀን 2013 ማይጠብሪ አዳርቃይ ነው። ከጎንደር ከተማ ውጭ በዳባት፣ በደምቢያና በሌሎች ወረዳዎች እንዲሁም ወረራ በተፈጸመባቸው በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች ጭምር እነዚህ የጎንደር ፋኖዎች ስለአማራ ከተሰውባቸው ቀናት በፊት፣ በወቅቱም ሆነ በኋላ ከብዙ አቅጣጫዎች ተነስተው በመዝመት ሲታገሉ የተሰው በርካታ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች እንዳሉ ይታወቃል። ይህን እንደ ማሳያ በሚል ተጠቀሰ እንጅ የአማራ ልጆች ስለ አማራ ክብር፣ ስለ ነጻነቱ፣ ስለ አጽመ እርስቱ ነፍሳቸውን ሳይሰስቱ ከአሸባሪ እና ወራሪ ኃይል ጋር ተዋድቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት ይሁን ይላል! ሁሉም ጀግኖች በየጊዜው እንዲዘከሩና እንዲታወሱም ይፈልጋል! ይጥራልም! የሰማዕታት ቤተሰቦችንም መጠየቅና መደገፍ በቀሪ ትውልድ ትክሻ ላይ የተጣለ ታላቅ አደራ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply