ትግሉ በፈጣን ድል እንዲደመደም እና ህዝባችንን ለማዳን ፋኖን በማገዝ ሂደት ላይ እንዴት መተባበር እንችላለን??? ========== ሸንቁጥ አየለ ========= በመላዉ አለም የተበተነዉ…

ትግሉ በፈጣን ድል እንዲደመደም እና ህዝባችንን ለማዳን ፋኖን በማገዝ ሂደት ላይ እንዴት መተባበር እንችላለን??? ========== ሸንቁጥ አየለ ========= በመላዉ አለም የተበተነዉ የፋኖ ደጋፊ የዲያስፖራ ሀይል ብንተባበር እኮ የፋኖን ትግል በጅጉ እናግዘዉ ነበር። በንግግር ሳይሆን በተጠና ስትራቴጅያዊ አካሂያድ በሚከተሉት መስኮች ማገዝ እንችላለን፥- 1፡ ከዬትኛዉም ቡድናዊ አካሂያድ ገለልተኛ በመሆን ሁሉም የፋኖ ሀይላት በገንዘብ፡ በስትራቴጅ፡ በጋራ ሰነድ ዝግጅት፡ በተቋማት ግንባታ እና በጋራ የሚመካከሩበት ሁኔታ እንዲፈጠር ማገዝ 2፡ፋኖ ባልተደራጀባቸዉ ልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ፋኖዎች እንዲፈጠሩ በማገዝ 3፡በመላ ሀገሪቱ ህዝባዊ አመጽ እንዲቀጣጠል በማገዝ 4፡ በመላ ሀገሪቱ ህዝብ ለኦነግ?/ኦህዴድ ታክስ አልከፍልም እንዲል 5፡ ፋኖዉ በፍጥነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆኖ እንዲወጣ 6፡ ፋኖ ማእከል እንዲሆን የሚስማሙ ተቃዋሚ ሀይላትን የሲቪል ማህበራትን የሚዲያ ልዩ ልዩ ቡድኖችን በማስተባበር የሽግግር መንግስት በፍጥነት ታዉጆ ቤተመንግስቱን ፋኖ እንዲቆጣጠረዉ ማስቻል ። ይሄም ምእራባዉያን ከኦነግ/ኦህዴድ ጋር ሆነዉ አንድ ሁለት የአማራ ሰዎችን በማሳተፍ ሽግግር መንግስት ተደረገ ለማለት የሚጎነጉኑትን የተንኮል የሽግግር መንግስት ህሳቤ ቆርጦ የሚጥል ይሆናል። ======== ለዉጥ ያለዉ ስራ መስራት የሚቻለዉ በመላዉ አለም የተበተነዉ የፋኖ ደጋፊ . የዲያስፖራ ሀይል ፡ የሲቪል ማህበራት ፡ የተቃዋሚ ስብስብ እንዲሁም የሚዲያ ሀይል በሙሉ ከተሳተፈበት ነዉ።ፈጣን፡ ዉል ያለዉ፡ በታላቅ ድል ፋኖ የጀመረዉን ተጋድሎ በሁል አቀፍ ዘርፍ የሚያግዝ ድጋፍ በመተባበር እና የተሻለ ስትራቴጂያዊ ስልት በመንደፍ ማድረግ ይቻላል። በጥቃቅን ልዩነት የማይለያይ እና ከምንም አይነት ወገንተኝነት የጸዳ ድጋፍ ለማድረግ የዉጭዉ ሀይል እንዴት መተባበር እንዳለበት መምከር መጀመር አለበት። ለምሆኑ ይሄ ሁሉ ሀይል እንዴትና በምን መልክ ሊተባበር ይችላል? ሀሳብ ስጡበት።ሃሳብ ስትሰጡ ልዩነቱ ላይ ሳይሆን አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ይተኮር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply