ትግራይን ከአፋር ክልል ጋር በሚያገናኙ አጠቃላይ የወረዳ መንገዶች መዘጋታቸውን የክልሉ መንግስት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ…

ትግራይን ከአፋር ክልል ጋር በሚያገናኙ አጠቃላይ የወረዳ መንገዶች መዘጋታቸውን የክልሉ መንግስት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

ትግራይን ከአፋር ክልል ጋር በሚያገናኙ አጠቃላይ የወረዳ መንገዶች መዘጋታቸውን የክልሉ መንግስት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአፋር ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሒም ኡመድ መሀመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ክልሉ ከዚህ ቀደም በህወሀት ሞግዚቶች ይመራ የነበረ በመሆኑ ጥቃቶች እንዳይከሰቱ ከኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ፤ ከብሔራዊ ደህንነት ፤ ፌደራል ፖሊስ እና የክልሉን የፀጥታ ሀይል ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ህወሀት ጥቃት ሊያደርስ ይችላል ተብለው የሚታሰቡ የክልሉ አካባቢዎች ተለይተው የፀጥታ ሀይሉ ሙሉ ቁጥጥር እያደረገባቸው እንደሚገኝም ሀላፊው ነግረውናል፡፡ ክልሉ ከዚህ ቀደም በህወሀት ሞግዚቶች ይመራ የነበረ በመሆኑ በዚህ ክልል ውስጥ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥቃት በመለየት አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ አቶ ኢብራሂም አክለውም ወደ ትግራይ ክልል የሚገቡ እና የሚወጡ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በአፋር ክልል የሚያልፉ መሆናቸውን ገልፀው አሁን የፀጥታ ሀይሎችን በመመደብ አዋሳኝ የወረዳ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲገደብ ተደርጓል፡፡ ጥብቅ ቁጥጥርም እየተከናወነ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡ በአፋር ክልል ውስጥ በሚገኙ የሀገር አቋራጭ መንገዶች ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል የሚል ጥርጣሬዎች በመኖራቸው በእያንዳንዱ ሀገር አቋራጭ መንገዶች መከላከያ ሰራዊቱን ጨምሮ የክልሉ ልዩ ሀይል ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ነው መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply