ትግራይ ውስጥ ታካሚዎች እየተጎዱ መሆኑ ተነገረ

ትግራይ ውስጥ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ታምመው በህክምና ተቋማት ውስጥ ክትትል ይደረግላቸው የነበሩ ክሃምሣ ሺህ በላይ ህሙማን በመድኃኒትና በህክምና እጦት ምክንያት ህይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንደሆኑ የተነገረው ዶ/ር ፀጋይ በሪሁ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በነገራችን ላይ፤ ፌደራሉ መንግሥት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ተበትኗል፤ ህገወጥ ነው ሲል ካወጀ ወዲህ አሁን ትግራይን እያስተዳደረ ላለው ኃይልም ሆነ ለቢሮዎቹና ለተቋማቱ ዕውቅና አይሰጥም።

በተለይ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ክልሉ የገባ ምንም መድኃኒትና የህክምና መሣሪያ እንደሌለ፤ በዚህ ምክንያት ታካሚዎችም ተገቢውን የጤና አገልግሎት እንደማያገኙ ዶ/ር ፀጋይ ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply