ትግራይ ውስጥ የወሲብ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሴቶችና ልጃገረዶች

https://gdb.voanews.com/A0B34EB6-FDEB-47C1-A3EF-9BEC2160F931_w800_h450.jpg

ትግራይ ውስጥ የመደፈር ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የሚናገሩ ከ580 በላይ ሴቶችና ልጃገረዶች በከባደ የአካልና የአዕምሮ ሥቃይ ላይ እንደሚገኙ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

እርዳታ ለማግኘት ወደተለያዩ የህክምና ተቋማት የሄዱት ተጎጂዎች ዕድሜያቸው ከስምንት ዓመት እስከ ዘጠና ዓመት እንደሚደርስ ከትግራይ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።

በተፈፀሙባቸው ጥቃቶች ለኤችአይቪና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች የተጋለጡ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውና ፅንስ ለማቋረጥ የተገደዱም እንደሚገኙባቸው ተገልጿል።

የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባችን ገብረ ገብረመድህን ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍስሃዬ ታቀርበዋለች። 

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply