ትጥቅ ለማስፈታት የተላኩ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ዋርካው ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች እና አባላት ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ! በዚህም ቆቦን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ከ…

ትጥቅ ለማስፈታት የተላኩ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ዋርካው ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች እና አባላት ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ! በዚህም ቆቦን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ከባድ ውጥረት መንገሱም ተመላክቷል። ታሕሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የፋኖ አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት እና ለማሰር የተላኩ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ዋርካው ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች እና አባላት ላይ ትናንት ታህሳስ 17/2015 ዓ/ም አመሻሹን ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸው የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።። ትናንት ታህሳስ 17/2015 ዓ/ም አመሻሹን ጀምሮ በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ጮቢ በር አከባቢ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎቹ አንድ የምስራቅ አማራ ፋኖ አባልን ባልታወቀ ምክኒያት አፍነው ለመውሰድ ሲሞክሩ ሌሎች የፋኖ አባላቱ የትግል ጓዳችንን አናስወስድም የሚል ምላሽ በመስጠታቸው በዚህ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ተኩስ ልውውጥ ማምራቱን ነው የአማራ ድምፅ ምንጮች ያረጋገጡት። ትናንት አመሻሹን ጀምሮ በጮቢ በር አከባቢ ከባድ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የገለፁት ምንጮቻችን፡አሁን ላይ ተኩሱ የቆመ ቢሆንም ነገር ግን ሁለቱም በየምሽጋቸው ሁነው ተፋጠው እንደሚገኙ አመላክተዋል። ዋርካው ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በስፍራው የሚገኙት እና ተኩስ የተከፈተባቸው ሌሎች የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ነገር ግን ከመንግስት የተላኩት የፀጥታ ኃይሎቹ አሻፈረኝ ማለታቸውን በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ አረጋግጠዋል። የፋኖ አባላትን ለማሰር የተላኩ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በምስራቅ አማራ ፋኖዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን የሰሙ የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ልጆቻችንን አትንኩብን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ከባድ ውጥረት መንገሱም ነው የተሰማው። በ ጌትነት አሻግሬ አማራ ድምፅ እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply