ቶም የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ለገበያ ካቀረብኳቸው ባይኮች ውስጥ 300 ያክሉ በህገወጥ መልኩ መንግስት አስሮብኛል አለ

በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና በገርዢ የመኪና እና የሞተር መገጣጠሚያ ያለው ቶም የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ በኤሌትሪክ የሚሰሩ ባይኮችን እየገጣጠምኩ ለገበያ ባቀርብም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከህግ አግባብ ውጪ ታርጋ የላቸውም በሚል ወደ 300 የሚሆኑ ደንበኞቼን ሳይክል አስሮብኛል ሲል ለፊደል ፖሰት ገልፇል።

ባይኮቹ በልዩ መለያ መስተናገድ አንደሚችሉ የትራንስፖርት ባለስልጣን ደብዳቤ ቢፅፍም ይሄን ወደ ጎን በመተው ባይኮቹን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እያሰረ መሆኑን የቶም የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ አቶ በረከት ተስፋዬ ተናግረዋል።

” የኢትዮጵያን በካይ ጭስ ለመቀነስ አስበን ነው በኤሌትሪክ የሚሰሩ በይኮችን እያመረትን ያለነው። ነገር ግን ገጣጥመን ሳይሆን ሰርቀን ያመጣን ይመስል ትራንስፖርት ቢሮው ሳይክሎቹን እያሰረ ነው ።ታርጋ የለውም ይሉናል ነገር ግን ከትራንስፖርት ባለስልጣን ለኤሌክትሪክ ባይክ መመሪያ ስላልተዘጋጀ ያለታርጋ ማሽከርከር ይችላሉ የሚል ደብዳቤ የተፃፈልን ሲሆን ደርጅቱ ልዪ መለያ ስጥቷቸው ባይኮቹ በመንገድ ላይ እያሉ ነው የታሰሩት ።”

” ኢ-ባይክ በተሽከርካሪ በካይ ጭስ የሚደርሰውን የከባቢ አየር ብክለትን፣ የጤና ቀውስ ለመቀነስ፣ አነስተኛ ፍጥነት ስላላቸው የትራፊክ አደጋን ይቀንሳሉ ብለን የሰራነው ልንበረታታ ሲገባን የዚህ አይነት ነገር መፈጠሩ ያሳዝናል ።” ብለዋል።

የትራንስፖርት ባለስልጣን ችግሩን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ህግን የተከተለ አካሄድ አየሄደ መሆኑን ገልፆ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር የመናበብ ችግር አንዳለ ገልፇል።

The post ቶም የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ለገበያ ካቀረብኳቸው ባይኮች ውስጥ 300 ያክሉ በህገወጥ መልኩ መንግስት አስሮብኛል አለ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply