ቶታል ኢነርጂስ ለ45 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የነዳጅ ማደያ መልሶ ገንብቶ አስመርቋል።ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቶታል ኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ መልሶ ግንባታ በዛሬው ዕለ…

ቶታል ኢነርጂስ ለ45 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የነዳጅ ማደያ መልሶ ገንብቶ አስመርቋል።

ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቶታል ኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ መልሶ ግንባታ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

ቦሌ መንገድ የሚገኘው የቶታል ኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት የቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስቶፍ ፌራ ገልጸዋል።

ለ45 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የቦሌ መንገድ ቶታል ኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ በመልሶ ግንባታው ብዙ አዳዲስ ጉዳዮች እንደተጨመረበትም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

የነዳጅ ማደያው የመያዝ አቅም ከ80 በመቶ ወደ 2መቶ በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ በመልሶ ግንባታው በአንድ ጊዜ ለ10 መኪኖች አገልግሎት መስጠት እንዲችል በአውሮፓ ስታንዳርድ መሰራቱን ገልጸዋል።

ነዳጅ ማደያው የራሱ የውሃ ጉድጓድ ያለው ሲሆን ፤ የተለያዩ አላርሞች እና ፍሳሽ ማስወገጃዎችም ተገጥመውለታል።

ነዳጅ ማደያው የስራ ቅጥሩን በ70 በመቶ ከፍ በማድረግ 22 አዳዲስ ሰራተኞችን መቅጠሩም ነው የተገለፀው።

ቶታል ኢነርጂስ በጥቂት ወራቶች ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያ ገጥሞ ወደስራ እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ቶታል ለ70 ዓመታት በኢትዮጵያ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከ2 ዓመት በፊት ስሙን ወደ ቶታል ኢነርጂስ ቀይሯል።

በምርቃት ስርዓቱ ላይ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የቶታል ኢነርጂስ ኢትዮጵያ አምባሳደር አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ፣ የፈረንሳይ አምባሳደርን ጨምሮ የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ተገኝተዋል።

ቶታል ኢነርጂስ ከ130 አገራት በላይ ማደያዎች ያሉት ሲሆን ለ105ሺህ ሰራተኞችም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

በእስከዳር ግርማ
መስከረም 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply