ቶጎ 145 ያህል መምህራን ከስራ አገደች፡፡

የሀገሪቱ የፑብሊክ ሰርቪስ ሚኒስትር በመንግስት ላይ ተቃውሞ እና አመጽ እንዲፈጠር አድርገዋል ያላቸውን መምህራን ሙሉ በሙሉ ከስራ ገበታቸው አግዷል ተብሏል፡፡

መምህራኑ ያነሱት ጥያቄ ከትምህርት ዘርፉ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለው እና የትምህርት ዘርፉን የሚጎዳ ተግባር ፈጽመዋል ሲል ነው መንግስት መምህሮችን የወቀሰው፡፡

የቶጎ የሲቭል ሰርቪስ ሚኒስትር ጊልበርት ባዋሬ ከስራ ገበታቸው የተባረሩት እነዚህ መምህራን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጥብቅ ግኑኝነት ያላቸው እና በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡

በዚችዉ ሀገር መምህራን ከትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን በመንግስት ላይ በተደጋጋሚ የሚያነሱ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስት ግን ጥያቄያቸው ፖለቲካዊ ነው ይላል፡፡

የትምህርት ፖሊሲው እንዲሻሻል፣ የመምህራን ክፍያ እንዲያድግ እና የመማሪያ ቦታ ሰላም እና ደህንነት እንዲጠበቅ በመምህራን በኩል በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

የሀገሪቱ ምንግስት እስከ ፈረንጆቹ 2025 ድረስ 3 ሺህ ተጨማሪ መምህራን እንደሚቀጥር አስታውቆ መምህራን የሚያገኙት ጥቅማ ጥቅምም በዚያው ልክ ያድጋል ብሏል፡፡

@አልጀዚራ

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply