ቻይና፤ የቡድን 7 አባል ሀገራት “ዓለምን መናቅ” አይችሉም ስትል ተቃወመች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቻይና ጉዳይ የሚደረግ ማን…

ቻይና፤ የቡድን 7 አባል ሀገራት “ዓለምን መናቅ” አይችሉም ስትል ተቃወመች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቻይና ጉዳይ የሚደረግ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት ያልተጠበቀ አደጋ እንደሚያስከትልም አስጠንቅቃለች። የቡድን 7 አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቡድን 7 አለም አቀፍ ጉዳዮችን በብቸኝነት የሚቆጣጠርበትና ሌሎች ሀገራትን የሚያንገላታበት ጊዜ አልፏል ብላለች። የቡድን 7 አባል ሀገራት በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የመግባት መብት እንደሌላቸው ቻይና አስታውቋለች። ቻይና ይህንን ያለችው የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ስብሰባ “ቤጂንግ አስገዳጅ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች” ትተገብራለች ሲሉ መተቸታቸውን ተከትሎ ነው። የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብሰባ ባስተናገደችው ብሪታኒያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፤ “ቡድን 7 አለም አቀፍ ጉዳዮችን በብቸኝነት የሚቆጣጠርበት እና ሌሎች ሀገራትን እንደፈለገ የሚያንገላታበት ጊዜ አልፏል” ብሏል። የሚመለከታቸው ሀገራት አለም አቀፍ ህግን እንዲያከብሩ ያሳሰበው መግለጫው፤ ቻይናን ማጣጣል፣ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባት እንዲሁም በቻይና እና በሌሎች አገሮች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ችግር መፍጠርን እንዲያቆሙ አሳስቧል። የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትሩዝ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብሰባ ዙሪያ በትናትናው እለት መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫውም “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቻይና አስገዳጅ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ ስጋታቸውን ገልፀዋል” ያሉ ሲሆን፤ በደቡብ ቻይና ባህር እና በታይዋን ባለው ውጥረት ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቀዋል። ቻይና በበኩሏ እነዚህ ጥያቄዎች አሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና ካናዳን በአባልነት ያቀፈው የቡድን ሰባት ጉዳይ አይደሉም የሚል አቋም ይዛለች። “በምስራቅ እና እና ደቡብ ቻይና ባህር ሁኔታ ላይ በውጭ ሀይሎች የሚደረግ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ያልተጠበቀ አደጋን ሊያስከትል ይችላል” በማለትም ቻይና አስጠንቅቃለች። የቻይና መንግስት በሀገሩ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በራሱ መንገድ ምክክር እና ድርድሮችን ተጠቅሞ እንደሚፈታም በብሪታኒያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ አስታውቋል ሲል አል ዐይን ዘግቧል። በተመድ ስብሰባ ሩሲያ፣ ቻይና እና ህንድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን መቃወማቸው ይታወሳል። ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በትዊተር ገፃቸው አሰፈሩት በሚል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ እንዳመለከተው ደግሞ አሜሪካ “በሽብር” ላይ አካሄድኩ ያለችው ጦርነት ብቻ ከ37 ሚሊዮን በላይ የአለም ዜጎችን አፈናቅሏል በ26 አመት ውስጥ 188 ጊዜ ወታደራዊ ጣልቃገብነትን በሃገራት ላይ ፈፅማለች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት በአሃዝ የተደገፈ መልዕክት የሜሪካካ ታሪክ የጣልቃገብነት ታሪክ መሆኑን ፤ ውጤቱም አጥፊ እንደሆነ መረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። አሜሪካ እንደ ሃገር ከቆመች ጀምሮ ካለው ጊዜ 92 በመቶውን በሌሎች ሃገራት ጣልቃ በመግባት ነው ያሳለፈችው ብለዋል ፤ ይህም ማለት ለሰላም ያዋለችው የእድሜዋን 20 በመቶ ነው ብለዋል ዋንግ ዌንቢን ሲቀጥሉ ከ1992 እስከ 2017 (እአአ) ያሉትን 26 አመታት በዋቢነት በማስቀመጥ በነዚህ ጊዜያት ውስጥ 188 ጊዜ አሜሪካ በተለያዩ ሃገራት ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ፈፅማለች ብለዋል። ይህ የወረራ እና የጦረኝነት ተግባር ውጤቱ ሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ የፀጥታ ፣ ማህበራዊ ችግርም ያስከተለ ነው። ቃል አቀባዩ በአህዝ አስደግፈው እንዳሰፈሩት እኤአ ከ2001 ወዲህ ብቻ አሜሪካ የፀረ ሽብር ዘመቻ በሚል በፈፀመቻቸው ጣልቃ ገብነቶች ከ37 ሚሊየን በላይ ህዝብ መኖሪያ አጥቶ ለስደት መዳረጉን አመልክተዋል። ዋንግ በ #nomore ወይም በበቃ ተቃውሞ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply