ቻይና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ዓለም አቀፍ ጉባኤዋ እንግዶቿን እየተቀበለች ናት

https://gdb.voanews.com/d10c7f40-a4f9-4775-8863-00213731c387_w800_h450.jpg

በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ዓለም አቀፍ ጎባኤ የምታካሒደው ቻይና፣ የ130 ሀገራት ተወካዮችን በመቀበል ላይ ናት፡፡ ጉባኤው፥ የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት ጥላ እንዳጠላበት፣ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

ቻይና፤ በጋዛ የሚካሔደውን ግጭት ለማርገብ ሚና እንድትጫወት ጥያቄ ሲቀርብላት ቆይቷል።

ዓለምን በመንገድ እና ተያያዥ መሠረተ ልማቶች ለማገናኘት ያቀደውና ቻይና “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” በሚል በወጠነችው ተነሣሽነት ላይ ተመሥርቶ በሚካሔደው ጉባኤ ከተጋበዙት ውስጥ፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገኙበታል። ለፑቲን፣ ከዩክሬን ወረራ ወዲህ የመጀመሪያ ጉዟቸው ይኾናል፤ ተብሏል።

ጉባኤው፣ ቻይና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ሚና ከፍ እንደሚያደርግ ቤጂንግ ተስፋ ብታደርግም፣ በጋዛ የሚካሔደው ግጭት ዓለም አቀፍ ትኩረትን እንደያዘ ይቀጥላል፤ ሲል ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።

ቻይና፤ ሐማስንና ሔዝቦላን ከምትደግፈው ኢራን ጋራ የሞቀ ግንኙነት አላት። የቤጂንግ ልዩ መልዕክተኛ ጃይ ጀን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

ነገ ማክሰኞ በሚጀምረው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የበርካታ ሀገራት መሪዎች፣ ዛሬ ቤጂንግ ገብተዋል። የሃንጋሪ፣ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ኬንያ እና ቺሊ መሪዎች ተጠቃሾቹ ናቸው።

ዛሬ ቤጂንግ የገቡት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ከቻይናው አቻቸው ጋራ ተወያይተዋል።

ቻይና፣ ቭላድሚር ፑቲንን የጉባኤው “ዋና እንግዳ” አድርጋ መሠየሟን ላቭሮቭ አድንቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply