ቻይና በሊጓ ላይ የደሞዝ የገደብ ጣሪያ አሰቀምጣለች

የእግርኳስ ባህሏን ለማሳደግ ጥረት ላይ የምትገኘው ቻይና ደጎስ ያለ ገንዘብ በስፖርቱ ላይ ፈሰስ በማድረግ ላይ ትገኛለች።በተለይ የእግርኳስ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋት እና በ2050 የአለም ዋንጫን ለማሳካት እየጠረች ትገኛለች።በሀገረ ቻይና ያለውን የደሞዝ ጣራን ለማሳካት ሲሉ  በርካታ ተጫዋቾች መዳረሻቸውን ወደዛው  እያደረጉ ይገኛሉ።

ዛሬ ላይ እየወጡ በሚገኙ  መረጃዎች መሠረት ቻይና ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የደሞዝ ጣራ አስቀምጫለሁ ብላለች።በሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን የሚጫወት  ከተለያየ ሀገር እና ክለብ የመጡ ተጫዋቾች በዓመት 3 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ደግሞ 2.7 ሚ ፓ እንዲያገኝ ውሳኔ አሳልፋለች  ሀገር በቀል ተጫዋች ደግሞ በዓመት እስከ 5 ሚሊዮን የን (571,000 ፓውንድ) ድረስ እንዲከፈለው ተወስኗል።ይህንን ህግ ተላልፎ የተገኘ ክለብ እስከ 24 ነጥብ ድረስ እንደሚቀነስበት ሲነገር ከተቀመጠው ገደብ ውጪም የሚከፈለው ተጫዋች ከቻይና እግርኳስ ማኅበር ውድድሮች እንደሚታገድ ተሰምቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply