ቻይና በታይዋን ድንበር አካባቢ አዲስ ወታደራዊ ልምምድ እንደምታደርግ ይፋ አደረገች።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 ቻይና በታይዋን ድንበር አካባቢ አዲስ ወታደራዊ ልምምድ እንደምታደርግ ይፋ አደረገች። የቻይና ጦር ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ያደረጉትን ጉብኝት በመቃወም ያደረገውን ግዙፍ ልምምድ ለማቆም እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ በታይዋን አቅራቢያ በባህርና በአየር ላይ አዲስ ወታደራዊ ልምምዶችን እንደሚጀመር አስታውቋል።

የቻይናው ምስራቃዊ ወታደራዊ እዝ በፀረ-ባህር ሰርጓጅ እና የባህር ላይ ጥቃት ላይ ያተኮረ ልምምድ እንደሚያካሂድ መናገሩ ቤጂንግ በታይዋን መከላከያ ላይ ጫና ማሳደሯን ትቀጥላለች የሚለውን ስጋት ከፍ አድርጎታል። የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ ቻይና ብስጭቷን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ሙከራ በማድረግ የገለጸች
ሲሆን ከዋሽንግተን ጋርም አንዳንድ የጋራ ስምምነቶችን እንድትሰርዝ አድርጓታል፡፡ አዲሱ ልምምድ የሚቆይበት ጊዜ እና ትክክለኛ ቦታ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ታይዋን ቀደም ሲል በደሴቷ ዙሪያ በነበሩት ስድስት የቻይናውያን የልምምድ አካባቢዎች አቅራቢያ የበረራ ገደቦችን ቃላልታለች ተብሏል። ዘገባው የሬውተርስ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply