ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ሽምግልና ልትጀምር ነው ቤጂንግ በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን ወደ ቀጠናው ሀገራት ለመላክ እየተዘጋጀች ነው፤ በኢኮኖሚ ልማት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደሚረዳ ቃል…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/t1OAMoyqu_c_VSJByk2aH2HVkUtNmddpYfJMelwbTGadn6gwPiAESnC6W2WFMmsv9UdFq52vpOpayEZG2owQQaEGCymChcFEnqpvR0MuASD751e0yIViCJrn7MO9TpmeINqKwD59mETCJbYrJoJmGQnVZJ9a-KfBQlZCo0-xevwUKqPMhvWMoCw3Y6D7zQ3ZwGqEF5UGm8_1UkX9sGon47_M38sFFvYvUwxYOKgNQX88IcTSUpPbI2RFs3zMDZyOyXuyxV8nf9k2SkUe7T6R7fGikl4FeYCLuArg1VXwz2lHkmcbNB6VfSqjYbYNyBHBhmCCXK_hRsfECI7oSU2TzA.jpg

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ሽምግልና ልትጀምር ነው

ቤጂንግ በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን ወደ ቀጠናው ሀገራት ለመላክ እየተዘጋጀች ነው፤ በኢኮኖሚ ልማት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደሚረዳ ቃል ገብታለች፡፡

በአንድ ወቅት በናይሮቢ የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት የነበሩት ሚስተር ዙ ቢንግ የቻይናን ሽምግልና ለመሞከር ወደ አፍሪካ ቀንድ በመመለስ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

በኤርትራ እና ኬንያ የሚያደርጉት ጉብኝት ባሳለፍነው ጥር ሃላፊነቱን ከተረከቡ በኋላ የመጀመሪያቸው ይሆናል ሲል ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ይህ የስራ ጉብኝት የረዥም ጊዜ ክልላዊ ሰላምን ፣ መረጋጋትን ፣ ደህንነትን እና ልማት ማምጣት ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረገው ገለጻ አሳውቋል ፡፡

“የአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የህዝብ ብዛት እና ትልቅ የእድገት እምቅ አቅም ባለው ጠቃሚ ቦታ ላይ ተቀምጧል። የቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ለመላው አፍሪካ ሰላም ፣ መረጋጋት ፣ ልማት እና ብልጽግና ትልቅ ፋይዳ አለው።”

‹‹ ዋናው አላማ የክልላዊ ሀገራት የጸጥታ፣ የልማት እና የአስተዳደር ሶስት ፈተናዎችን በገለልተኛ አቀራረቦች እንዲቋቋሙ እና የረጅም ጊዜ መረጋጋትን እና ልማትን እና ብልጽግናን ማስመዝገብ ነው›› ብለዋል ዙ ቢንግ በመንግስት ለሚተዳደረው ግሎባል ታይምስ የተባለ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚታተም የሀገሪቱ ጋዜጣ፡፡

ልዩ መልክተኛው በዚህ ሳምንት በናይሮቢ ፣ አስመራ እና አዲስ አበባ ጉዟቸውን እንደሚጀምሩም ተናግረዋል፡፡

ይህ አካባቢ የአለማችን ሀያል ሀገራት አይን ማረፊያ ሆኗል.፤ እኛም በዚያ ስላለው ነገር በቅረበት እንከታተላለን ብለዋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply