ቻይና በፈረንጆቹ 2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከሪዎችን ቁጥር በ20 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 ቻይና በፈረንጆቹ 2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከሪዎችን ቁጥር በ20 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ ተነገረ፡፡ቻይና ታዳሽ ሃይል የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎችን በሚመለከት ከፈረምጆቹ 2021 እስከ 2035 ለመተግበር ያወጣችውን እቅድ ይፋ ያደረገች ሲሆን ይህም በዘርፉ እመርታን ለማምጣት በእጅጉ ይረዳታል ነው የተባለው፡፡

ሀገሪቱ በዘርፉ ያስቀመጠችው እቅድ የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅምን ማጎልበት፣ ከአከባቢ ብክለት ጋር የሚስማሙ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋትና ማልማትን ያካትላል ነው የተባለው፡፡በዘርፉ አዲስ የተቀመጠው ግብ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች በ12 ኪሎዋት እስከ 100 ኪሎ ሜትር እንዲጓዙ የሚያስችል ሲሆን በ2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ቁጥር በ20 በመቶ ማሳደግ ይገኝበታል፡፡

በተጨማሪም በ2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች በዋነኛነት የአዲስ የቤት መኪናዎችን ሽያጭ እንዲቆጣጠሩ የሚደረግ ሲሆን ሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ቀስ በቀስ በኤሌክትሪክ የመቀየር ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ዓለም አቀፉን ገበያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ፈጠራ የተቆጣጠረችው ቻይና ዘርፉ ከሚከናወነው ሽያጭ 55 በመቶ ድርሻ መያዟንም ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply