ቻይና አሜሪካን አስጠነቀቀች፡፡አሜሪካ ከጠብ አጫሪነቷ የማትቆጠብ ከሆነ የመልስ ምት እንደሚጠብቃት ቻይና አሳስባለች፡፡የቻይና የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃለ አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በሰጡት መ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/elWvS3ur2bBr2ahDEkS-VEd7TQ_zi3idxYQM7189UllDC7K53WZmkrn8oBEzdDqTsY5x5a5V0sMcDNVN0V8cfo-wQueanFhUkdk_lzoVRu19paXm3Lp-iAClNZ9hMpQBwuBTQ4NpdZqkjdd2Ye3ODe9M0ov-4HGXXqJpitvjrPqgfGIZMTRj8PrDQ-m40u4vgg2nWs4uoYw3sqLgjybOSVHrawBhO1YVjNeySwp3DEloEw71EGs3bjCwxHAtKonT2tQXjRNanirkcD8lD5XxHJMEGYTAk7Uk1R_6I_HRNAtfZH5JYrUewio4-qNb4lIGyxbL5f2NRzwnrqIZ93Ht7Q.jpg

ቻይና አሜሪካን አስጠነቀቀች፡፡

አሜሪካ ከጠብ አጫሪነቷ የማትቆጠብ ከሆነ የመልስ ምት እንደሚጠብቃት ቻይና አሳስባለች፡፡

የቻይና የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃለ አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ አንድ ተጨማሪ ቅስቀሳ ካደረገች ቻይና ቁርጠኛ የሆነ የመልስ ምት ትሰጣለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በቅርቡ ያደረጉት የታይዋን ጉብኝት፣ የአንድ ቻይና ፖሊሲን የሚጻረር ቅስቀሳ መሆኑን ቃል አቀባዩ አስታዉሰዋል፡፡
አሜሪካ ጊዜዉ ከማለፉ በፊት ታይዋንን ለመበዝበዝ ቻይናን መጠቀም ማቆም አለባት ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

የፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎ ቻይና እያደረገች ያለዉ ወታደራዊ ልምምድ ምክኒያታዊ እና ያልተጋነነ ነዉ ማለታቸዉን ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply