ቻይና ውስጥ 133 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን መከስከሱን የቻይና መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ ንበረት የሆነው ይህ ቦይን 737 ወድቆ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/kIym2qh-R1LIemSXvN2T9b-v19PlwihPafVqtdlgpto3AP8mKU90kpiRe51PMR71PWtf0_njDNQmL2_NKRJE_QoZpFPImLmVKYPCIpumfFK7SVl12oN-UUio0lpB1ehY4rqS7HnNwJ1f3d5Q9NxxGQ7Kfqug0DS09bHJvY19bBoH6rvSQhcOFVoevD2FwEb_w1mde0v-BGFvPpCPkN_t5bY4ICRgro7ge0tj8YBpuDNVRC5vTaVWTmVryLe4UO8uQAFssdVd0ufh8FAvadjWb_0dPjRh0_MY0b8XUsZJyYaXGC6-5dwb8ZUk469u82TLLS75pYNhYdvYQyjS9QCh3w.jpg

ቻይና ውስጥ 133 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን መከስከሱን የቻይና መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ ንበረት የሆነው ይህ ቦይን 737 ወድቆ መከስከሱ የተነገረው ጓንግዡ ግዛት ውስጥ ነው።

አስካሁን በአደጋው ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች የታወቀ ነገር የለም።

የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አውሮፕላኑ ወድቆ የተከሰከሰው በተራራማ አካባቢ ሲሆን በስፍራው ባለ ጫካ ላይ እሳት ተነስቷል።

ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በበረራ ቁጥር ኤምዩ5735 በቻይና የሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ቀን በኋላ ከኩንሚንግ ተነስቶ ወደ ጓንግዡ እያመራ ነበር ተብሏል።

የቻይና ብሔራዊ ቴሌቪዥን የነፍስ አድን ሠራተኞች ወደ የአደጋው ስፍራ መሰማራታቸውን ተዘግቧል።

አውሮፕላኑ ዉዡ በሚባለው የቻይና ግዛት ውስጥ ቴንግ በሚባል አካባቢ መከስከሱ ተዘግቧል።

ጉዋንግዢ የቻይና ደቡባዊ ግዛት ስትሆን በደቡብ ምሥራቅ ቻይና ውስጥ ከምትገኘው ዋነኛዋ ከተማ ጉዋንግዡ ጋር ተጎራብታ ትገኛለች።

በበይነ መረብ ላይ የበረራ መስመሮችን የሚያሳዩ ድረ ገጾች የአውሮፕላኑ ያለበትን ስፍራ “ያልታወቀ” በማለት እያመላከቱ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply