ቻይና የአሜሪካ-እንግሊዝ-አውስትራሊያ ስምምነትን ኃላፊነት የጎደለው በማለት ኮንናለችቻይና በአሜሪካ ፣ በእንግሊዝ እና በአውስትራሊያ መካከል የተደረገውን ታሪካዊ የደህንነት ስምምነት “እጅግ…

https://cdn4.telesco.pe/file/X7tSO1-eIQu4BkrJobCUSZf5YzRQFh1eNnjIuaC2ngpjkLwPpniU_espVf1h9T2ijjeScYj3AkF2htuUnDi74e6DQz9NIXlnyRQGKYa8bvVmZU7ubotGdsBteibqcL5yQp1XMAfcj7fj6M_w5f5501L4aYuMBw_rNMpHvZYr1t3ieY5oFaPFsR9Or3t-9kzuu44VCtpPu4vfrGi5CO9YTn5Xeui96cl0m9OLBZfAJmYIlAV_EZ3tJFF1QvkIqVAnym24PHpE2uQMEq0beE3tI0YM13vvcnesZ58EEY7hwpxPo3_-9ZY_M0RaZwLTdQ8587wkL4FJJrMiJxZ_T7bxYw.jpg

ቻይና የአሜሪካ-እንግሊዝ-አውስትራሊያ ስምምነትን ኃላፊነት የጎደለው በማለት ኮንናለች

ቻይና በአሜሪካ ፣ በእንግሊዝ እና በአውስትራሊያ መካከል የተደረገውን ታሪካዊ የደህንነት ስምምነት “እጅግ ኃላፊነት የጎደለው” እና “ጠባብ አስተሳሰብ” በማለት ገልፃለች።

በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ እና እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በኑክሌር ኃይል የሚሠሩ የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ለመሥራት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂን ለአውስትራሊያ ይሰጣሉ።

ሶስቱ ሀገራት ያደረጉት ስምምነት በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ የቻይናን ተፅእኖ ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተሰምቷል።

ቀጠናው ለዓመታት የሀይል ሚዛን ማሳያ ሆኖ የቆየ ሲሆን እዚያ ያለው ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን እንዳሉት ህብረቱ “የአካባቢያዊ ሰላምን በእጅጉ ይጎዳል … እና የመሳሪያ ውድድሩን ያጠናክራል” ብለዋል።

‹‹ ጊዜው ያለፈበት የቀዝቃዛው ጦርነት … አስተሳሰብ ›› ብለው የጠሩትን ስምምነት ተችተው ሦስቱ አገሮች “የራሳቸውን ጥቅም እየጎዱ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የቻይና መንግስታዊ ሚዲያዎች ስምምነቱን የሚያወግዙ ተመሳሳይ ርዕሶችን የያዙ ሲሆን በግሎባል ታይምስ ጋዜጣ ላይ አውስትራሊያ አሁን “እራሷን የቻይና ጠላት አድርጋለች” ብሏል።

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply