ቻይና የኮቪድ-19 መነሻን የሚመረምሩ ሰዎችን ቪዛ መከልከሏ ተገለጸ፡፡

ከኮቪድ-19 ጋራ በተያያዘ የአለም ጤና ድርጅት አንድ የመርማሪዎች ቡድን ወደ ቻይና ለመላክ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር ተብሏል፡፡ሆኖም ቻይና ባልታወቀ ምክንያት ለዚህ ቡድን የመግቢያ ቪዛ ከልክላለች የተባለ ሲሆን ሁለት የምርመራ ቡድን አባላትም ጉዞ ከጀመሩ በኋላ እንዲመለሱ መደረጉ ተገልፃል፡፡ለረዥም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ይህ አጣሪ ቡድን ወደ ቻይና የማምራት ጉዳይ ላይ ስምምነት የተደረሰው ባለፈው ታህሳስ ወር እንደ ነበረ ይታወቃል፡፡የአለም ጤና ድርጅት ዋና ሃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቻይና የቪዛ ጉዳይን በጊዜ ማጠናቀቅ አለመቻሏ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ገልፀዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply