ችግር ያለባቸው አከባቢዎችን መሰረት አድርገው በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚለቀቁ ጽሁፎች ትክክለኛ ምንጭና እውነታ ላይ ሊመሠረቱ ይገባቸዋል ተብሏል።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ስነ ተግባቦት መምህሩ አቶ ሰለሞን ሙሉ ለአሀዱ እንደገለፁት የማህበረሰብ አንቂዎችም ሆኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች ችግር ያለባቸውን አከባቢዎች መሰረት አድርገው የሚፅፉት ፅሁፍ በህብረተሰቡና በሀገር ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ሀላፊነት መውሰድ ይገባቸዋል ብለዋል።

በተለያዩ ክልሎች ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ላይ ያሉና ለመሄድ የተዘጋጁ ተማሪዎች በመኖራቸው በማህበራዊ ትስስር ገፆች በሚለቀቁ መረጃዎች ወላጆችና ተማሪዎች ሊሸበሩና ወዳልተገባ ድርጊት ስለሚሄዱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።

በመሆኑ ችግር ባለባቸው አከባቢዎች መንግስት ሀላፊነት ወስዶ ሙሉ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።የቀድሞ አንጋፋ የጋዜጠኝነት መምህሩ አቶ ማህረጉ በዛብህ በአብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም መረጃን የሚለቁ ሰዎች ምንጭ፣ ተአማኒነትና ህብረተሰቡ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ታሳቢ ባለማድረጋቸው ችግር ሲፈጥሩ ይስተዋላል ብለዋል።

በመሆኑ ህብረተሰቡ መረጃን ከተአማኝ ምንጭ መውሰድ ይኖርበታል ብለዋል።

ቀን 28/10/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply