“ነሃሴ 12 የታላላቅ መሪዎቻችን የልደት መሆኑን አስመልክቶ በተለያየ ክንውኖች አስበነው እንውላለን” የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 11 ቀን…

“ነሃሴ 12 የታላላቅ መሪዎቻችን የልደት መሆኑን አስመልክቶ በተለያየ ክንውኖች አስበነው እንውላለን” የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ነሀሴ 12 የእምዬ ሚኒልክ ፣የእቴጌ ጣይቱ እና የፊት አውራሪ ገበየሁ ልደት ቀን መሆኑን የጠቀሰው የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር በዓሉን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታስቦ እንደሚውል ገልጧል። የአፄ ልብነ ድንግል ልጅ ከሆኑት ከአፄ ያዕቆብ ትውልድ 13ኛ የዘር ሀረግ የሆኑት እምዬ ምኒልክ ነሃሴ 12 ቀን በ1836 ዓ.ም በአማራ ምድር በሸዋ ክፍለ ሀገር በአንኮበር ነው የተወለዱት። አያታቸው ሳህለስላሴ የሸዋውን ንጉስ ሐይለመለኮትን ይወልዳሉ፤ ሐይለ መለኮት ደግሞ ወ/ሮ እጅግአየሁን ያገቡና ልጅ ምኒልክ ይወልዳሉ። ነሃሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም የተወለዱት ልጅ ምኒልክ በ11 ዓመታቸው አፄ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ በመጡ ጊዜ ይዘዋቸው ወደ ጎንደር ሄደው ነበር። “ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ” በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት ጣይቱ አባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለማሪያም ፤ እናታቸው ወ/ሮ የውብዳር ይባላሉ። የተወለዱት ነሃሴ 12 1832 ዓ.ም ነው ። የጦሩ ጀነራል ገበየሁ ካሳ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ግዛት በአንጎለላ ነው የተወለዱት። ክርስትና የተነሱትም በአፄ ናኦድ ዘመነ መንግስት በተቆረቆረችው የአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ነው። እርሳቸው “በጦርነት ስዋጋ በጥይት ተመትቼ ብወድቅ የተመታሁት ጀርባዬን ከሆነ ስሸሽ ነው አሞራ ይብላኝ እዛው ተውኝ ፤ ግንባሬን ከተመታሁ ግን ሃገሬ ቅበሩኝ ” ብለው መናገራቸው ታሪክ መዝግቦታል። በአድዋ ጦርነት ለተገኘው አኩሪ ድል የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙ የጦር መሪ ነበሩ ያለው ማህበሩ ተእነዚህን ታላላቅ መሪዎች የልደት ቀን በተለያየ ክንውኖች አስበነው እንውላለን ብሏል። ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ደማቅ ታሪክ ሰርተው ፤ አገር ሰርተው ላስረከቡን ቀደምት አማራ አያቶቻችን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply