ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ሕይዎታቸውን ያጡ ሰማዕታት በሁመራ ከተማ እየታሰቡ ነው፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ሕይዎታቸውን ያጡ ሰማዕታት በሁመራ ከተማ እየታሰቡ ነው፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” በሚል መሪ መልዕክት ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በጠዋቱ ወጣቶች በባሕር ዳር ከተማ ጎዳናዎች የአማራን ሕዝብ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የማንነትና የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ አንግበው የተነሱ ወጣቶች ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ በነበረው ሕዝባዊ ሰልፍ መስዋእት ሆነዋል፤ በርካቶች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። የለውጡን ሰማዕታት ለመዘከር ከባሕር ዳር የመጡ ልዑካን አባላት በሁመራ ከተማ በጠዋቱ ችግኝ ተክለዋል። ወጣቶቹን ለመዘከር የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት፣ የአደራ ቃል ርክክብ እና ልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply