You are currently viewing ነበልባሉ ፋኖ :- የእራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ አባላት  በጀብዱ የህዝብ እንባ ሲያብስ  ————————————— የአማራ ህዝብ ትግል ዘርፈ ብዙ ምክን…

ነበልባሉ ፋኖ :- የእራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ አባላት በጀብዱ የህዝብ እንባ ሲያብስ ————————————— የአማራ ህዝብ ትግል ዘርፈ ብዙ ምክን…

ነበልባሉ ፋኖ :- የእራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ አባላት በጀብዱ የህዝብ እንባ ሲያብስ ————————————— የአማራ ህዝብ ትግል ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች አሉት:: ዋነኛው ግን የመኖር እና ያለመኖር ፣የባርነትና የነፃነት፣ወደ ቀድሞ አባቶቹ ክብር የመመለስ ጉዳይ ብሎም በሀገሩ በኢትዮጵያ እንደ ሰዉ የመኖር ጥያቄ ጭምር ነዉ::ይሄን የተረዳዉ ፋኖም የአማራንህዝብ ህልዉና ለማረጋገጥ ብሎም የኢትዮጵያን ነጻነት እዉን ለማድረግ ከፍተና ተጋድሎ ላይ ነዉ::የፋኖ መሪዎችም ከጣና በሰፋ የረጋ አስተሳሰብ እንዲሁም ከአፋሩ ኤርታሌ በላይ በሚፋጅ ቁጭት መስዋዕት እየሆኑ ህዝባቸዉንም እያታገሉ ይገኛሉ:: ———– የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማጥፋት የተነሳዉ የአቢይ ዐህመድ መራሹ የኦነግ/ኦህዴድ ዐረመኔ ሰራዊት ሰሞኑ…ን በሰሜን ሸዋ ሞረትና ጅሩ እነዋሪ ከተማ ለገበያ የወጣውን ወጣት:ሽማግሌ : አዛዉንት እና ሴት ሲያስር እና ሲደበድብ ውሏል:: ለክረምት ምርት የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ከገበሬው መኪና እያስቆመ እና እህያ እየፈታ ሲዘርፍ ውሏል::የህዝብ ገንዘብ ሲዘርፍ:የነጋዴ መጋዘን ሲዘርፍ ከእናቶች መቀነት እያስፈታ ገንዘባቸዉን ሲገፍ ሰንብቷል:: ይሄ አረመኔ የአቢይ ሰራዊት ከፈጸመዉ ግፍ አንዱን ለመጥቀስ ወንድወሰን የተባለዉን ጎልማሳ “ና ተፈተሽ ” ብለዉ በግፍ መደብደብ እና ማሰቃዬት ይጀምራሉ:: ወንድወሰን የተባለዉም ጎልማሳ ምን አልታጠቅሁም: ሰላማዊ ሰዉ ነኝ: ወይም የበደልኩት ሰዉ የለም: ምኔን ነው እምትፈትሹት? ምን አድርጌ ነዉ የምታሰቃዩኝ ሲል” ጥያቄ ያቀርባል::ወንጀለኛዉ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊትም በሌሎች ዜጎች ላይ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ወንድወሰንን በመሳሪያ ሰደፍ መደብደብ: በወንድወሰን አካል ላይ ግፍ መፈጸም እና ማሰቃዬቱን ይቀጥላል:: በባዶ እጁ የነበረዉ ወንድወሰንም በሚደርስበት ግፍ በመበሳጨት 3ቱን የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት በባዶ እጁ ያለምንም ጦር መሳሪያ በቦከስ ብቻ ነስር በነስር አድርጎ ብትንትናቸውን ያወጣቸዋል:: በዚህም የተደናገጠዉ አረመኔው የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት ተጨማሪ ሀይል በማሰማራት ለገበያ የመጣዉን ህዝብ እና የከተማዉን ነዋሪ ማሰቃዬት በስፋት ግፍ መፈጸሙን ይቀጥላል:: በየፌርማታውም የለየለት ፍተሻ በማድረግ ህዝብ በመዝረፍ: በመደብደብ እና በማፈን ስራ ላይ መሰማራቱን አጠናክሮ ይያያዘዋል:: ===== ነበልባሉ ፋኖ በወገኑ ላይ የሚደረገዉን ግፍ ሰማ::የህዝብንም እንባ በጀብዱ አበሰዉ —————————- ይሄን የህዝቡን በደል የሰማው የራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ፋኖ አባላት ወደ ከተማዉ በደፈጣ እና በቆረጣ በመግባት በህዝብ ላይ ግፍ የሚያደርሰዉን የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጥተዉታል:: መውጫ መግቢያ በማሳጣትም የፋሽስቱን ሰራዊት በታትነው የህዝብ ልጅነታቸውን አረጋግጠዋል። ይሄን መብረቃዊ ኦፕሬሽን የተመለከተው አረመኔዉ የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊትም ከተማ ገበያዉ ህዝብ መሀል በመግባት ማህበረሰቡ እንዲጎዳ ውጊያው በገበያ መሀል ለማድረግ ቢያቅድም ለህዝባቸው የሚጨነቁት የሀቅ ታጋዮች ግን በብልጠት የጠላትን ሀሳብ አክሽፈው የአብይ አህመድ ሰራዊትን ወደ ዳር በመሳብ ወቅጠዉታል።በዚህ የደፈጣ ዉጊያ ብሎም ጠላትን ወደ መታረጃዉ የመሳብ ስልታዊ የወታደራዊ ጥበብ የተጠና አካሂያድ የተካነዉ ነበልባሉ ፋኖ የጠላትን አከርካሪ የመስበር ስራዉን ቀጥሎበታል:: ====== የመረጃ ምንጭ:- የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር እራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ናደው ሻለቃ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ምኒልክ ማንደፍሮ

Source: Link to the Post

Leave a Reply