<<እንዳትፈቷቸው>> ነውረኞች *************************** ታሕሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) ሊቀ መንበር እሸቱ ጌትነትን ጨምሮ…

<<እንዳትፈቷቸው>> ነውረኞች *************************** ታሕሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) ሊቀ መንበር እሸቱ ጌትነትን ጨምሮ ከባሕር ዳር ወደ መተማ ተወስደው በዚያ ታስረው የሚገኙ 5ቱ የግፍ እስረኞች ሲቀርቡባቸው የነበሩት የ<በሬ ወለደ> ክሶች በሙሉ ውድቅ መደረጋቸውን ተከትሎ ባቀረቡት የአካል ነጻ መውጣት አቤቱታ የምዕራብ ዞን ፍርድ ቤት ትናንት ታኅሣሥ 21/2015 ዓ.ም እያንዳንዳቸው በአምስት ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ወስኖ ነበር። ነገር ግን ክፍያውና አጠቃላይ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ <<ዛሬ ስለመሸ ነገ ጠዋት ይፈታሉ>> በሚል እንዲያድሩ ከተደረገ በኋላ ዛሬ ታኅሣሥ 22/2015 ዓ.ም ጠዋት እንዲፈቱ ሲጠየቅ ከዞኑ ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ከክልል(ከበላይ) <እንዳትፈቷቸው> ስለተባልኩ አልፈታም የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። ይህም በአማራ ሕዝብ ላይ የትኛውንም ነውር ከመሥራት የሚያግድ ሕግ ላለመኖሩ ማሳያ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ነውር ነውረኞች እስካሉ ድረስ የሚቀጥል መሆኑ ታውቆ ዋጋ ከፍሎ ፍትሕን እና ነጻነትን ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ይሆናል። ነጻነት በነጻ አይገኝም!!! ታኅሣሥ ፳፪/፳፻፲፭ ዓ.ም የአማራ ተማሪዎች ማህበራዊ (አተማ) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply