ነገ “ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል የሚዘከረውን ዕለት በማስመልከት የሚከናወኑ መርሃ ግብሮች ይፉ ተደረጉ

ዕረቡ ጥቅምት 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት ላይ ጥቅምት 24/2013 ያደረሰውን ጥቃት መታሰቢያ በማስመልከት “ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል የሚዘከረውን ዕለት አስመልክቶ የሚከናወኑ መርሃ ግብሮችን የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ይፉ አድርጓል።

የከተማ አሰተዳደሩ መርሃ ግብሮቹን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ፤ ዕለቱን ኹሉም የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ነዋሪው ሕዝብ በተመሳሳይ ኹኔታ በሚከተለው መልኩ የሚዘከር ይሆናል ብሏል።

በዚህም መሰረት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ኹሉም ተሽከርካሪዎች ለአንድ ደቂቃ ክላክስ እንደሚያሰሙ ተገልጿል።

ከጠዋቱ 4:30 በተመሳሳይ ሰዓት ኹሉም በከተማዋ የሚገኙ የመንግስትና የግል ተቋማት አመራሮች፣ ሰራተኞች እና መላው ነዋሪ በተሰማራበት እና ባለበት ቦታ በመቆም የቀኝ እጁን በግራ ደረቱ ላይ በማድረግ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳም” በማለት ለሰማዕታቱ ያለውን ክብር የሚገልፅ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር አስታውቋል።

The post ነገ “ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል የሚዘከረውን ዕለት በማስመልከት የሚከናወኑ መርሃ ግብሮች ይፉ ተደረጉ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply