ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ወደ አረምነት እየተቀየረ ነው ተባለ፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና በኦሮሚያ ክልል መሀከል የሚገኘው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል፡፡ፓርኩን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/FLrObTjaOzitgltOZkK7RkkXLzdyvbo20NlpZnNfUS_GY_0hPX6RZ3xhMCTliJk914mYv7OtKGiEGTtXfadCt5zBHOXBEMuyPGuZ3tnI3iKdMjJubtVyp4x_UWQ3Sg3-nXr7WrsVLPd8ZQpFOmk8ErhL2f28gFDJThmHJ5aizzcyo7kVWI8WAPXl2q9_LdQmEhchaMhY1QznDmx4NKy5mN5pvupEPkQxztPT0QOT-wGTHxxVQed_BZr9XR6_SzrtIh1oOz-IRY6awuCOEy0V6YPbrMFEpsdVY5BH9ZHIGnGpmNQaSELArFhV5rjbK6_ATEhmWc6gdNaoPOQ84Ch2XA.jpg

ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ወደ አረምነት እየተቀየረ ነው ተባለ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና በኦሮሚያ ክልል መሀከል የሚገኘው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል፡፡

ፓርኩን የሚያዋስኑት ሁለቱ ክልሎች ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው የተነሳ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ነው የተነገረው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያዳመጠ ባለው የቱሪዝም ሚኒስቴር የ 9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ለነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ትኩረት እንደሲሰጠው ተጠይቋል፡፡

በፓርኩ ከሚገኘው 52 ነጥብ ሁለት ሜዳማ የግጦሽ መሬት 51 በመቶውን ማለትም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በፓርኩ ውስጥ ነዋሪ በሆኑ የምዕራብ ጉጂ ገላና ወረዳ ኤርጌንሳ ቀበሌ አርብቶ አደሮች በመቶ ሽሕ በሚቆጠሩ ከብቶቻቸው በመጋጡ በፓርኩ ያሉ የዱር እንሰሳት ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል ነው የተባለው፡፡

የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ 514 km2 ላይ ያረፈ ከአዲስ አበባ 507 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በውስጡ 351 የአእዋፍ 16 የዓሳ እንዲሁም ከ91 በላይ አጥቢ እንሰሳትን የያዘ ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡

በፓርኩ የሚገኙ የዱር እንሰሳት የሜዳ አህያ የሜዳ ፍየል እንዲሁም የመሳሰሉት ከስማቸው መነሳት እንደሚቻለው ሜዳማ በሆነ ስፍራ ውስጥ ብቻ መኖር የሚችሉ በመሆናቸው አሁን የፓርኩ ሜዳማ ስፍራ በከብቶች ግጦሽ ምክንያት መውደሙን ነው የተገለጸው፡፡፡

የፓርኩ ሳራማ አካሉ ወደ ቁጥቋጧማ ስፍራ እየተቀየረ በመጤ አረም እየተወረረ ስለመጣ የዱር እንሰሳቱ መኖር የሚችሉት ሳራማ እንጂ ቁጥቋጧማ ስፍራ ውስጥ ባለመሆኑ ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply