You are currently viewing “ነፃነት ናፈቀኝ! ፤ አያሸንፉኝም አሸንፋቸዋለሁ።”       ታዲዎስ ታንቱ  የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)…    ግንቦት 16/2015 ዓ/ም       አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጤ ሲያስባ…

“ነፃነት ናፈቀኝ! ፤ አያሸንፉኝም አሸንፋቸዋለሁ።” ታዲዎስ ታንቱ የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ግንቦት 16/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጤ ሲያስባ…

“ነፃነት ናፈቀኝ! ፤ አያሸንፉኝም አሸንፋቸዋለሁ።” ታዲዎስ ታንቱ የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ግንቦት 16/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጤ ሲያስባቸው የነበሩት የታሪክ አዋቂ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱን ቂሊንጦ ሄጄ ለማየት በፓስፖርት መታወቂያ ችግር መጠየቅ አልቻልኩም ነበር። ግንቦት 16 ቀን 2015 በፍርድ ቤት ቀጠሮ ላገኛቸው በጠዋት ከቤቴ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት አቀናሁ፤ ጋሽ ታዲዎስ ከፊት ለፊት ከጠበቃቸው ታለማ ጋር ተቀምጠው ድንገት አገኘዋቸው። በእጅጉ የከበረ ሰላምታ ተለዋውጠን ችሎቱን ለመታደም ቁጭ አልኩኝ፤ ከጠበቃቸው ታለማ ውጭ ማንም ሰዉ በፍ/ቤት የለም፤ ጋዜጠኛ የለም፤ ሲናገሩ የሚያደንቋቸው አድናቂዎች ዛሬ የሉም በቃ የኛ ትግል ማሳያ ነበሩ። ዐቃቢ ህግ ባስገባው የመከላከያ ምስክሮች አሰማም መቋረጥ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 25/ 2015 ዓ/ም ጠዋት ቀጠሯቸዉ ችሎት ሲያልቅ እኔም ከአዳራሹ ወጣሁ። ጋሽ ታዲዮስ በፖሊስ ተከበው ወደ ብረቷ ቤት እስረኞች ማቆያ ቦታ ወሰዷቸው ትንሽ ጠጋ ብዬ ለማነጋገር መልካም ሰዉ አንዱ ፖሊስ ፈቀደልኝ … ጥያቄ_ ጋሽ ታዲዎስ ጤናዎት እንዴት ነው? ጋሽ ታዲዎስ_ደህና ነኝ እግዚያአብሔር ይመስገን። ጋሽ ታዲዎስ እርስዎ ጠንካራ ነዎት ብርታትዎ እኛንም ያበረታል። ጋሽ ታዲዎስ_ጥሩ አመሰግናለሁ። ጥያቄ_የማስተላልፈው የሚናገሩት መልዕክት አለዎት? ጋሽ ታዲዎስ_ስለራሴ የማወራው ምንም የለም፤ ነፃነት ግን ናፈቀኝ! “አዎ ነፃነት ይናፍቃል! ለነፃነታችሁ ታገሉ እኔ እየታገልኩ ነው “አያሸንፉኝም አሸንፋቸዋለሁ።” እሺ ጋሽ ታዲዮስ ፈጣሪ ያበርታዎ አንተም በርታ እሺ እበረታለሁ! ተለያየን ። እሳቸውን እያየሁ ምንም እንዳላበረከትኩ ተሰማኝ፤ እውነት ዋጋዋ ከባድ ናት በዚህ የእርጅና እድሜ መሰቃየት ለማን ብለዉ? በአዕምሮዬ ከራሴ ጋር ተሟገትኩ ታጋዩና ትግሉ መቼ ይሆን በቁጭት የሚገናኙት “የኛ ነገር.. ስንታዬሁ ቸኮል በችሎት ተገኝቶ ያጋራው ትዝብት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply