ኑሯቸውን በውጭ ሃገር ያደረጉ የመርዓዊ እና እካባቢዋ ተወላጆች ያወጡት የአቋም መግለጫ:- ===========//============ ታጋይ ዘመነ ካሴን ማሰር የክልል ወጣቶችን ተስፋ እንደማሰር…

ኑሯቸውን በውጭ ሃገር ያደረጉ የመርዓዊ እና እካባቢዋ ተወላጆች ያወጡት የአቋም መግለጫ:- ===========//============ ታጋይ ዘመነ ካሴን ማሰር የክልል ወጣቶችን ተስፋ እንደማሰር ይቆጠራልና በአስቸኳይ ይፈታ እንላለን! ኗሪነታችንን በውጭ አገር ያደረግን የመርዓዊ እና አካባቢዋ ተወላጆች የሜጫ ህብረት በተባለ ማህበር ስም ተሰባስበን የወጣንበትን ማህበረሰብ በተለያዩ የልማት ስራዎች ስንደግፍ ቆይተናል:: ባለፈው አመት የትግራይ ወራሪ ሃይል ወደ ክልላችን ገብቶ በህዝባችን ላይ ግፍ በፈፀመበት ወቅት ደግሞ ከአባላቶቻችን በርካታ ገንዘብ አሰባስበን ወደ ሀገር ቤት በመላክ ለህልውና ትግሉ የበኩላችንን ድጋፍ አድርገናል:: በዚህ ድጋፋችን ለሃገር መከላከያ : የአማራ ልዩ ሃይል: ፋኖ እና ሚሊሻ የሚሆን የስንቅ ያቀረብን ሲሆን ለውስን የዘማች ቤተሰቦች ደግሞ የገንዘብ ድጎማ አድርገናል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጁት ትህነግ እና ኦነግ ሸኔ የዐማራን ህዝብ ከሚኖርበት ቦታ ሳይቀር እያሳደዱ መግደላቸው ሳያንስ ዛሬ ላይ በይፋ በጠላትነት ፈርጀው የሚንቀሳቀሱ የህዝባችን ደመኛ ጠላቶች መሆናቸው ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት እንኳን ትህነግ በወረራ ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚገኙ አማራዎች ላይ የግፍ ብትሩን እያሳረፈ ያለ ሲሆን ኦነግ ሸኔ ደግሞ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ኗሪ የሆኑ ንፁሃን አማራዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨፈጨፈ ይገኛል። ይህም እኩይ ድርጊት እንደ ማህበረሰብ ልባችንን ሰብሮታል። እነዚህ ድርጅቶች ለእኩይ ተግባራቸው የሚገባቸውን ቅጣት የሚያገኙበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን:: በተጨማሪም በንፁሃን አማራዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በቀጠለበት በዚህ ሰዓት መንግስት ስለ “ሰላም መስፈን” እና ስለ “ልማት መስፋፋት” ሲያወራ መስማት በህዝባችን ሰቆቃ ላይ እንደመሳለቅ አድርገን እንወስደዋለን:: የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን:: ህዝባችን በትህነግ እና በኦነግ ሸኔ (ኦነግ) እየተሰነዘረበት ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል በማሰብ የክልላችን ወጣቶች በፋኖ መዋቅር ታቅፈው የሚያደርጉትን አበረታች እንቅስቃሴ ከመደገፍ አኳያ የክልሉ መንግስት የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ ሲገባው በተቃራኒው ወጣቶቹን በማሳደድ እና አደረጃጀታቸውንም በመበተን ላይ ተጠምዶ ይገኛል። ይህ ፀረ-አማራ ተግባር ለክልሉ ህዝብ እቆረቆራለሁ በሚል አካል መፈፀሙን ስንመለከት እንደ ህዝብ እጅግ ፈታኝ ቀውስ ውስጥ መግባታችን እንገነዘባለን። ለህዝባችን አንድነት እና ሰላም ይበጃል በሚል የቀረበለትን የሽምግልና ጥሪ ተቀብሎ ባህር ዳር ከተማ ተገኝቶ በነበረው የአማራ ህዝባዊ ሃይል መሪ ታጋይ ዘመነ ካሴ ላይ ሰሞኑን የተፈፀመው የአፈና እስር የማህበራችንን አባላት በእጅጉ ያሳዘነ እና ያስቆጣ ፀያፍ ተግባር ሆኖ አግንተነዋል። በዚህ የክህደት ተግባር ላይ ተሳትፎ የነበራችሁን አካላት ሁሉ አምርረን እናወግዛለን:: በዚህ ተግባር ውስጥ ተሳትፎ የነበራችሁ ግለሰቦች ማንነታችሁ ተለይቶ ታውቆ በተሳትፏችሁ ልክ ተጠያቂ የምትሆኑበት ቀን እሩቅ አይሆንም:: ይህም ይሳካ ዘንድ ማህበራችን ከሌሎች ለአማራ ህዝብ የሚቆረቆሩ አካላት ጋር በመተባበር የሚሰራ መሆኑን እንገልፃለ:: ታጋይ ዘመነ ካሴን ከእስር መፍታት ለዝባችን አንድነት ጉልህ አስተዋፆ ከማበርከት ባሻገር ወጣቱን በሰፊው አነቃንቆ የህልውና ትግሉን እንዲቀላቀል ከማድረግ አኳያ ላቅ ያለ ጠቀሜታ ስለሚኖረው ዘመነ በአስቸካይ ከእስር ይፈታ ዘንድ በአፅንዖት እንጠይቃለን:: ወንድማችን ሳይውል ሳያድር ከእስር ተፈቶ ሁላችንም አትኩሮታችንን ወደ ህልውና ትግሉ እና ወደ ልማት እንድንመልስ ይሁን እያልን ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን! በመጨረሻም የህዝባችን አንድነት የሚያላሉ እና ተስፋውንም የሚያጨልሙ መሰል ድርጊቶች ደግመው እንዳይፈፀሙ እናሳስባለን:: አማራ በክንዱ ህልውናውን ያረጋግጣል! የሜጫ ህብረት ማህበር መስከረም 17 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply