“ኑ በጋራ በወቢቷ ባህር ዳር የፍቅርና የአንድነት ማዕድ እንጋራ” ክቡር ዶክተር ድረስ ሳህሉ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 20 ቀን 20…

“ኑ በጋራ በወቢቷ ባህር ዳር የፍቅርና የአንድነት ማዕድ እንጋራ” ክቡር ዶክተር ድረስ ሳህሉ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ የሆኑት ዶክተር ድረስ ሳህሉ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃችው ለገና እና ለጥምቀት በዓል ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በወቢቷ ባህር ዳር ከተማ በታሪካዊ ቤተ መንግስት የፍቅርና የአንድነት ማዕድ እንጋራ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ በውቢቷ ባህርዳር የተዘጋጀ ልዩ ዝግጅት በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር ጥር 4/2014 ዓ/ም አባይ ዳር በሚገኘው በአፄ ሃይለ ስላሴ ቤተመንግሥት በቤዛዊት ተራራ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ማለትም ከሰዓት በኃላ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተዘጋጅተዋል። በዝግጅቱ ላይ ለሀገር ወዳድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ልዩ ምስጋና ይቀርባል። ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በዲፕሎማሲው በኩል ለነበራቸው ተሳትፎ እና በሁሉ አቅጣጫ ላደረጉት ድጋፍ ሁሉ ምስጋና ይቀርባል። በወቅታዊ ጉዳዮች፣በከተማችን ልማትና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ውይይት ይደረጋል። የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ይቀርባሉ። በመጨረሻም ለክብር እንግዶቻችን የእራት ግብዣ ይደረጋል። በዕለቱ ውድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ዲያስፖራዎች ሁሉ በክብር ተጋብዛችኃል። ለዚህ ታሪካዊ የፍቅር፣የአንድነት፣የኢትዮጵያዊነት ማዕድ ማካፍል የምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በመሉ ወደፊት በገፃችን በምናወጣችው መመዝገቢያ ቦታዎች፣አድራሻዎች በቀጥታም ይሁን በተወካይ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ ስንል በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች!! የባህር ዳር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply