You are currently viewing “ኑ ከሞቀ ቤታቸው ተባረው ጎዳና ወጥተው እየተራቡ ያሉ ወገኖቻችንን እንመግብ” የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር  መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የባህር ዳር ከ…

“ኑ ከሞቀ ቤታቸው ተባረው ጎዳና ወጥተው እየተራቡ ያሉ ወገኖቻችንን እንመግብ” የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የባህር ዳር ከ…

“ኑ ከሞቀ ቤታቸው ተባረው ጎዳና ወጥተው እየተራቡ ያሉ ወገኖቻችንን እንመግብ” የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር ከኦሮሚያ ክልል እና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በጎጃም በተለያዩ ቦታዎችና በደብረ ብርሀን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናቶች የሚዘልቅ የምግብ እህል የማሰባሰብ ዘመቻ ይጀምራል። የባህር ዳር ከተማ የበጎ/አድ/ማህበር ከዚህ በፊት ከመተከል ተፈናቅለው ራንች ካምፕ ለሚገኙና ሰቆጣ ከተማ ላይ በካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አሰባስቦ በመውሰድ እዛው ውሎ በማደር ለተፈናቃዮች ማከፋፈሉ አይዘነጋም። አሁንም ከዛሬ መጋቢት 20/ 2015 ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናቶች በባህር ዳር ከተማ 5 ቦታዎች ላይ ድንኳን በመጣል የምግብ እህል እና የንፅህና መጠበቂያ የሚሆኑ ግብአቶችን መሰብሰብ ይጀምራል። በመሆኑም በባህር ዳር ከተማ የምትገኙ ወገኖቻችን በተጣሉት ድንኳኖች በአይነት ይዛችሁ እንድትመጡ ፣ ከባህር ዳር ውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን በማህበሩ ህጋዊ አካውንት ገንዘብ በማስገባት የበኩላችሁን እንድትወጡ ማህበሩ ይጠይቃል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply