
“ኑ ከሞቀ ቤታቸው ተባረው ጎዳና ወጥተው እየተራቡ ያሉ ወገኖቻችንን እንመግብ” የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባህር ዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማህበር ከኦሮሚያ ክልል እና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በጎጃም በተለያዩ ቦታዎችና በደብረ ብርሀን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናቶች የሚዘልቅ የምግብ እህል የማሰባሰብ ዘመቻ ይጀምራል። የባህር ዳር ከተማ የበጎ/አድ/ማህበር ከዚህ በፊት ከመተከል ተፈናቅለው ራንች ካምፕ ለሚገኙና ሰቆጣ ከተማ ላይ በካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አሰባስቦ በመውሰድ እዛው ውሎ በማደር ለተፈናቃዮች ማከፋፈሉ አይዘነጋም። አሁንም ከፊታችን መጋቢት 20/ 2015 ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናቶች በባህር ዳር ከተማ 5 ቦታዎች ላይ ድንኳን በመጣል የምግብ እህል እና የንፅህና መጠበቂያ የሚሆኑ ግብአቶችን መሰብሰብ ይጀምራል። በመሆኑም በባህር ዳር ከተማ የምትገኙ ወገኖቻችን በተጣሉት ድንኳኖች በአይነት ይዛችሁ እንድትመጡ ፣ ከባህር ዳር ውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን በማህበሩ ህጋዊ አካውንት ገንዘብ በማስገባት የበኩላችሁን እንድትወጡ ማህበሩ ይጠይቃል።
Source: Link to the Post