ኑ የአቅመ ደካሞችን ቤት እንስራ-ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በአዲስ አበባ የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት እንጀምራለን አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት የሚሆን የመደመር መንገድ መጽሐፍ ተሽጦ ካስገኘው ገንዘብ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ብር መመደባቸውን አስታውቀው ሁሉም ዜጋ በእድሳት መርኃ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በማዕድ ማጋራት እንዲሁም ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ያማከለ ተመጣጣኝ የኑሮ እርከን መፍጠር እንዲቻል ከአመራሩ በቀጣይ የሚጠበቁ ኃላፊነቶችን ጠቁመዋል፡፡ ቤት ኪራይ ጭማሪ ላይ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮፐርቲ ታክስ ላይ ደሃውን ታሳቢ ያደረገ አሰራር መዘርጋት እንደሚጠበቅም አሳስበዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply