ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡
በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ከተቋሙ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ኃላፊ ኢሬኔ ዱኩምዌናዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በውይይቱ አምባሳደር መለስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተወሰደ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንፃር ኒስክ ካፒታል በኢንቨስትመንት ለመሰማራት እድሉ እንዳለው ገልጸዋል።
ኢሬኔ ዱኩምዌናዮም የፋይናንስ ተቋሙ በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስችል ሰፊ የፋይናንስ አቅም እንዳለው መግለፃቸውን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ባንኩ ኬንያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ ሃገራት ጽህፈት ቤቱን ከፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply