ኒዉ ዮርክ በሚገኘዉ ዶናልድ ትራምፕ በነበሩበት ችሎት ፊት ለፊት አንድ ግለሰብ እራሱን ማቃጠሉ ተሰምቷል።

የትራምፕ የወንጀል ችሎት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ከፍርድ ቤቱ ዉጪ በሚገኝ መናፈሻ ዉስጥ አንድ ወጣት ራሱን አቃጥሏል፡፡

ሰዉዬዉ ይህንን ድርጊት ለምን እንደፈፀመም ሆነ በምን ሁኔታ ዉስጥ እንዳለ ማወቅ አልተቻለም።

ወጣቱ ራሱን ያቃጠለው ምናልባትም በትራምፕ ላይ እየቀረቡ ካሉ ክሶች በላይ በአሜሪካና በተለያዩ ሃገራት ንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ግፎች ይገዝፋሉ፤ለእነርሱ ግን ፍትህ የሚሰጥ የለም የሚለውን ለማመላከት ነው በሚል በቅርብ ሰዎቹ እንደተነገረ ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ በ2016 ምርጫ ከማሸነፋቸዉ በፊት በወሰብ ፊልም ከምትታወቀው ስቶርሚ ዳኒልስ ግንኙነት እንደነበራቸውና ይህንን ለመደበቅም የ130ሺህ ዶላር ገንዘብ ለመክፈል ሞክረዋል በሚል ነበር ክስ የተመሰረተባቸው።
ይሁን እንጂ ዶናልድ ትራምፕ ክሳቸዉን ክደዉ ተከራክረዋል።

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply